ስለዚህ ሰዎቹ ለመሄድ ተነሥተው ከሳኦል በፊት ወደ ዚፍ ሄዱ፤ በዚህ ጊዜ ዳዊትና ሰዎቹ ከየሴሞን በስተ ደቡብ በዓረባ ውስጥ ባለው በማዖን ምድረ በዳ ነበሩ።
ማዖን፣ ቀርሜሎስ፣ ዚፍ፣ ዩጣ
የሚደበቅባቸውን ቦታዎች ሁሉ ካያችሁ በኋላ ግልጽ መረጃ ይዛችሁ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም አብሬችሁ እሄዳለሁ፤ ብቻ በዚያ አገር ይገኝ እንጂ በይሁዳ ነገዶች ሁሉ መካከል ከገባበት ጕድጓድ ገብቼ አወጣዋለሁ።”
ሳኦልና ሰዎቹም ዳዊትን ሊፈልጉት ሄዱ፤ እርሱም ይህን በሰማ ጊዜ፣ ወደ ዐለቱ ወርዶ በማዖን ምድረ በዳ ተቀመጠ። ሳኦልም ይህን እንደ ሰማ፣ ዳዊትን በማሳደድ ወደ ማዖን ምድረ በዳ ዘልቆ ገባ።
በማዖን ምድር በቀርሜሎስ ንብረት ያለው አንድ ባለጠጋ ሰው ነበረ፤ እርሱም አንድ ሺሕ ፍየሎችና በቀርሜሎስ የሚሸልታቸው ሦስት ሺሕ በጎች ነበሩት።