አሁንም ሂዱና አጣሩ ዘወትር የት እንደ ሆነና በዚያ ያየውን ሰው ለይታችሁ ዕወቁ፤ እጅግ ተንኰለኛ መሆኑን ሰምቻለሁና።
እነሆ፤ አሁን እንኳ በአንዱ ዋሻ ወይም በሌላ ቦታ ተደብቆ ይሆናል። እርሱ ቀድሞ አደጋ በመጣል ከሰዎችህ ጥቂት ቢሞቱ ይህን የሰማ ሁሉ፣ ‘አቤሴሎምን የተከተለው ሰራዊት ዐለቀ’ ብሎ ያወራል።
ንጉሡም፣ “ሰዎች ልኬ እንዳስይዘው፣ የት እንደሚገኝ ፈልጉ” ሲል አዘዘ። ከዚያም፣ “በዶታይን ይገኛል” የሚል ዜና ደረሰው።
ጥበበኞችን በራሳቸው ተንኰል ይይዛቸዋል፤ የጠማሞችንም ሤራ ያጠፋል።
ሳኦል እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ለእኔ ስለ ተቈረቈራችሁ እግዚአብሔር ይባርካችሁ፤
የሚደበቅባቸውን ቦታዎች ሁሉ ካያችሁ በኋላ ግልጽ መረጃ ይዛችሁ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም አብሬችሁ እሄዳለሁ፤ ብቻ በዚያ አገር ይገኝ እንጂ በይሁዳ ነገዶች ሁሉ መካከል ከገባበት ጕድጓድ ገብቼ አወጣዋለሁ።”
በኬብሮን እንዲሁም ዳዊትና ሰዎቹ በተዘዋወሩባቸው ስፍራዎች ሁሉ ለነበሩት ላከላቸው።