Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



1 ሳሙኤል 18:9

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከዚያች ዕለት አንሥቶ ሳኦል ዳዊትን በቅናት ዐይን ይመለከተው ጀመር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

11 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የላባ አመለካከት ከቀድሞው የተለወጠበት መሆኑንም ያዕቆብ ተረዳ።

ንዴት ጨካኝ፣ ቍጣም ጐርፍ ነው፤ በቅናት ፊት ግን ማን መቆም ይችላል?

እንዲሁም ጥረትና የሥራ መከናወን ሁሉ ሰው በባልንጀራው ላይ ካለው ቅናት እንደሚመነጭ ተመለከትሁ፤ ይህም ደግሞ ከንቱ፣ ነፋስንም እንደ መከተል ነው።

ታዲያ በራሴ ገንዘብ የፈለግሁትን ማድረግ አልችልምን? ወይስ ቸር በመሆኔ ምቀኛነት ያዘህን?’

መስገብገብ፣ ክፋት፣ ማታለል፣ መዳራት፣ ምቀኛነት፣ ስም ማጥፋት፣ ትዕቢት፣ ስንፍና ናቸው።

ለዲያብሎስም ስፍራ አትስጡት።

ወንድሞች ሆይ፤ እርስ በርሳችሁ አታጕረምርሙ፤ አለዚያ ይፈረድባችኋል፤ እነሆ፤ ፈራጁ በበር ላይ ቆሟል።

በማግስቱም ከእግዚአብሔር የታዘዘ ክፉ መንፈስ በሳኦል ላይ በኀይል መጣበት፣ በዚህ ጊዜ ዳዊት ወትሮ እንደሚያደርገው ሁሉ በገና ሲደረድር፣ ሳኦል በቤቱ ሆኖ ትንቢት ይናገር ነበር። ሳኦል በእጁ ጦር ይዞ ነበር፤

ሳኦል እጅግ ተቈጣ፤ ይህም ነገር አላስደሰተውም። እርሱም፣ “ለዳዊት ዐሥር ሺሕ አሉለት፤ ለእኔ ግን ሺሕ ብቻ! እንግዲህ መንግሥት እንጂ ሌላ ምን ቀረው” አለ።

ሳኦል ዳዊትን እንዲገድሉት ለልጁ ለዮናታንና ለባልሟሎቹ ነገራቸው። ዮናታን ግን ዳዊትን እጅግ ይወድደው ነበር፣




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች