አንድ ቀን የሳኦል ልጅ ዮናታን ወጣት ጋሻ ጃግሬውን፣ “ና በሌላ በኩል ወዳለው የፍልስጥኤማውያን ጦር ሰፈር እንሻገር” አለው። ይህን ግን ለአባቱ አልነገረውም ነበር።
ባልንጀራህን አትመን፤ በጓደኛህም አትታመን፤ በዕቅፍህ ለምትተኛዋ እንኳ፣ ስለምትነግራት ቃል ተጠንቀቅ።
በዚህ ጊዜ የእግዚአብሔር መንፈስ በኀይል ወረደበት፤ ስለዚህ የፍየል ጠቦት እንደሚገነጣጠል አንበሳውን ያለ ምንም መሣሪያ በባዶ እጁ ገነጣጠለው፤ ያደረገውን ግን ለአባቱም ሆነ ለእናቱ አልነገራቸውም ነበር።
በእጁ ወስዶም መንገድ ለመንገድ እየበላ ሄደ፤ ከወላጆቹም ጋራ እንደ ተገናኘም ከማሩ ሰጣቸው፤ እነርሱም በሉ። ነገር ግን ማሩን የወሰደው ከአንበሳ በድን መሆኑን አልነገራቸውም ነበር።
ጌዴዎን ከአገልጋዮቹ ዐሥር ሰዎች ወስዶ እግዚአብሔር እንዳዘዘው አደረገ፤ ቤተ ሰቡንና የከተማውን ሰው ስለ ፈራ ይህን ያደረገው ቀን ሳይሆን ሌሊት ነበር።
ሳኦል ከእስራኤል ሦስት ሺሕ ሰዎች መረጠ። ሁለቱ ሺሕ በማክማስና በኰረብታማው አገር በቤቴል ከሳኦል ጋራ፣ አንዱ ሺሕ ደግሞ በብንያም ግዛት በጊብዓ ከዮናታን ጋራ ነበሩ። የቀሩትን ሰዎች ግን ወደ የቤታቸው እንዲሄዱ አሰናበተ።
ስለዚህ ጦርነቱ በተደረገበት ዕለት ከሳኦልና ከልጁ ከዮናታን በቀር፣ ዐብረዋቸው ከነበሩት ወታደሮች መካከል ሰይፍ ወይም ጦር የያዘ አንድም ሰው አልነበረም።
በዚያ ጊዜ አንድ የፍልስጥኤማውያን ጭፍራ ወደ ማክማስ መተላለፊያ ወጥቶ ነበር።
ሳኦልም በጊብዓ ዳርቻ ሚግሮን በተባለ ስፍራ ከአንድ የሮማን ዛፍ ሥር ሰፍሮ ነበር፤ ስድስት መቶ ያህል ሰዎችም ዐብረውት ነበሩ፤
ከዚያም አገልጋዮቿን፣ “ቀድማችሁኝ ሂዱ፤ እኔም እከተላችኋለሁ” አለቻቸው፤ ለባሏ ለናባል ግን አልነገረችውም።