ከዚያም ሳሙኤል ለሕዝቡ እንዲህ አለ፤ “ሙሴንና አሮንን የመረጠ፣ የቀድሞ አባቶቻችሁንም ከግብጽ ያወጣ እግዚአብሔር ነው።
ባሪያውን ሙሴን፣ የመረጠውንም አሮንን ላከ።
ዐለቱን ሰነጠቀ፤ ውሃም ተንዶለደለ፤ እንደ ወንዝም በበረሓ ፈሰሰ።
ሙሴና አሮን ካህናቱ ከሆኑት መካከል ነበሩ፤ ሳሙኤልም ስሙን ከጠሩት መካከል አንዱ ነበረ፤ እነርሱ ወደ እግዚአብሔር ተጣሩ፤ እርሱም መለሰላቸው።
እግዚአብሔር “እስራኤላውያንን በየሰራዊታቸው ከግብጽ አውጡ” ብሎ የነገራቸው አሮንንና ሙሴን ነበር።
ስለ እስራኤላውያን ከግብጽ መውጣት፣ የግብጽን ንጉሥ ፈርዖንን ያናገሩትም እነዚሁ ሙሴና አሮን ነበሩ።
እግዚአብሔር በነቢይ አማካይነት እስራኤልን ከግብጽ አወጣ፤ በነቢይም በኩል ተንከባከበው።
ከግብጽ አወጣሁህ፤ ከባርነት ምድርም ተቤዠሁህ፤ እንዲመሩህ ሙሴን፣ አሮንንና ማርያምን ላክሁልህ።