እነዚህም ሰሎሞን የሚያሠራውን ሥራ የሚያከናውኑትን ሠራተኞች የሚቈጣጠሩ አለቆች ናቸው፤ ቍጥራቸውም ዐምስት መቶ ዐምሳ ነበር።
እንዲሁም ሰሎሞን ሥራውን የሚቈጣጠሩ ሦስት ሺሕ ሦስት መቶ ኀላፊዎች ነበሩ።
ከእነዚህም ሰባ ሺሑን ተሸካሚዎች፣ ሰማንያ ሺሑን በኰረብታው ላይ ድንጋይ ፈላጮች፣ ሦስት ሺሕ ስድስት መቶውን ደግሞ የሥራው ተቈጣጣሪዎች ሆነው ሰዎቹን እንዲያሠሩ መደበ።
ከእነዚህም ሁለት መቶ ዐምሳዎቹ የንጉሥ ሰሎሞን ሹማምት ሰዎቹን የሚቈጣጠሩ ነበሩ።