እርሱም፣ “ወንድሜ ሆይ፤ እነዚህ የሰጠኸኝ ከተሞች ምንድን ናቸው?” አለ፤ እነዚህንም “ከቡል ምድር” አላቸው፤ እስከ ዛሬም በዚሁ ስም ይጠራሉ።
ይሁን እንጂ ኪራም ከጢሮስ ተነሥቶ ሰሎሞን የሰጠውን ከተሞች ለማየት በሄደ ጊዜ አልተደሰተባቸውም፤
እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ “ስለ ሦስቱ የጢሮስ ኀጢአት፣ ይልቁንም ስለ አራቱ፣ ቍጣዬን አልመልስም። የወንድማማችነትን ቃል ኪዳን በማፍረስ፣ ሕዝቡን ሁሉ ማርካ ለኤዶም ሸጣለችና።
ከዚያም በምሥራቅ በኩል ወደ ቤትዳጎን ይመለስና ዛብሎንንና የይፍታሕኤልን ሸለቆ ይዞ፣ ካቡልን በስተግራ በመተው በሰሜን በኩል ወደ ቤትዔሜቅና ወደ ንዒኤል ያቀናል።