ሰሎሞን ከብዛታቸው የተነሣ እነዚህ ሁሉ ዕቃዎች እንዲመዘኑ አላደረገም፣ ስለዚህም የናሱ ክብደት ምን ያህል እንደ ነበር አልታወቀም።
እንዲሁም ምንቸቶቹን፣ መጫሪያዎቹን፣ መኰስተሪያዎቹን፣ ጭልፋዎቹን፣ በአጠቃላይም ከናስ የተሠሩትን የቤተ መቅደሱን መገልገያ ዕቃዎች ሁሉ ወሰዱ።
ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መገልገያ ብሎ ከናስ ያሠራቸው ሁለት ዐምዶች፣ ትልቁ የውሃ ገንዳ፤ ተንቀሳቃሽ የዕቃ ማስቀመጫዎች ክብደታቸው ከሚዛን በላይ ነበር።
“ለእግዚአብሔር ቤት እንዲሆንም አንድ ሺሕ መክሊት ወርቅ፣ አንድ ሚሊዮን መክሊት ብር፣ ከብዛቱ የተነሣ ሊመዘን የማይቻል ናስና ብረት ለማዘጋጀት በተቻለኝ ሁሉ ጥሬአለሁ፤ በተረፈ አንተ ጨምርበት።
እነዚህም ቍጥራቸው እጅግ የበዛ የወርቅ፣ የብር፣ የናስና የብረት ሠራተኞች ናቸው። በል ሥራህን ጀምር፤ እግዚአብሔርም ከአንተ ጋራ ይሁን።”
ለቅጥር በሮቹ ምስማርና ማጠፊያ የሚሆን ብዙ ብረትና ከብዛቱ የተነሣ ሊመዘን የማይቻል ናስ አዘጋጀ።
እነዚህ ሰሎሞን ያሠራቸው ነገሮች ሁሉ እጅግ ብዙዎች ስለ ሆኑ የናሱ ክብደት ምን ያህል እንደ ነበር አልታወቀም።
ንጉሥ ሰሎሞን ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ከናስ ያሠራቸው፦ ሁለቱ ዐምዶች፣ ትልቁ የውሃ ገንዳ፣ ከሥሩ ያሉት ዐሥራ ሁለት ወይፈኖችና ተንቀሳቃሽ ማስቀመጫዎች ክብደታቸው ከሚዛን በላይ ነበር።