በአዕማዱ ጫፎች ላይ ያሉትን ባለሳሕን ቅርጽ ጕልላቶች የሚሸፍኑና በሁለት ረድፍ የተቀረጹትን መረቦች የሚያስጌጡትን አራት መቶ ሮማኖች፤
በሁለቱም የምሰሶ ጕልላቶችና ከመርበቡ ቀጥሎ ባለው የክብ ቅርጽ ላይ ዙሪያውን በሙሉ ሁለት መቶ ሮማኖች በተርታ ነበሩ።
ሁለቱን አዕማድ፣ በአዕማዱ ጫፎች ላይ ያሉትን ሁለት ባለሳሕን ጕልላቶችን፤ በአዕማዱ ላይ ያሉትን ባለሳሕን ቅርጽ ሁለት ጕልላቶችን ያስጌጡትን ሁለት መረቦች፤
ዐሥሩን የዕቃ ማስቀመጫዎች፣ ከዐሥር መታጠቢያ ገንዳዎቻቸው ጋራ፤
በአንዱ ዐምድ ዐናት ላይ ያለው የናስ ጕልላት ቁመት ዐምስት ክንድ ሲሆን፣ ዙሪያውንም ሁሉ የሮማን ቅርጽ ባላቸው የናስ ጌጣጌጦች የተዋበ ነበር፤ ሌላውም ዐምድ የሮማኑን ጌጣጌጥ ጨምሮ ከዚሁ ጋራ ተመሳሳይ ነበር።