በዋናው ቤተ መቅደስና በቅድስተ ቅዱሳኑ ግድግዳ ዙሪያ ልዩ ክፍሎች ያሉት ተቀጥላ ግንብ ሠራ።
በቤተ መቅደሱም ውስጥ በስተኋላ በኩል፣ ሃያውን ክንድ ቅድስተ ቅዱሳን እንዲሆን፣ ከወለሉ አንሥቶ እስከ ጣራው ድረስ በዝግባ ሳንቃዎች ጋረደው፤
ለቅድስተ ቅዱሳኑም መግቢያ የወይራ ዕንጨት ደጃፎች ሠራ፤ መቃኖቻቸውንና መድረኮቻቸውን ባለዐምስት ማእዘን አደረገ።
የምድር ቤቱ ወርድ ዐምስት ክንድ፣ የመካከለኛው ፎቅ ስድስት ክንድ፣ የሦስተኛው ፎቅ ሰባት ክንድ ነበር፤ የቤተ መቅደሱን ግድግዳ ዘልቆ እንዳይገባም፣ ከቤተ መቅደሱ ግንብ ውጭ ዙሪያውን እርከኖች አደረገ።
የሌዋውያኑ ተግባር በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አገልግሎት የአሮንን ዘሮች መርዳት፣ የቤተ መቅደሱን ቅጥር ግቢና ክፍሎች መከባከብ፣ የተቀደሱ ዕቃዎችን ሁሉ ማንጻትና በእግዚአብሔር ቤት ያሉትን ሌሎች ተግባሮች ማከናወን ነበር።
ከዚያም ዳዊት የቤተ መቅደሱን መመላለሻ፣ የሕንጻውን፣ የዕቃ ቤቶቹን፣ የፎቁንና የውስጥ ክፍሎቹን እንዲሁም የማስተስረያውን ቦታ ንድፍ ለልጁ ለሰሎሞን ሰጠው።
ሌዋውያን የነበሩት አራቱ የበር ጠባቂ አለቆች ግን በእግዚአብሔር ቤት ውስጥ የሚገኙትን ክፍሎችና ግምጃ ቤቶች በኀላፊነት ይጠብቁ ነበር።
ሕዝቅያስም በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ ጐተራ እንዲያዘጋጁ አዘዛቸው፤ እነርሱም አዘጋጁ።
በተሰጠው መመሪያ መሠረት፣ በቅድስተ ቅዱሳኑ ፊት ለፊት እንዲነድዱ፣ ከንጹሕ ወርቅ የተሠሩ መቅረዞች ከነቀንዲሎቻቸው፣
ከዚያም ካህናቱ የእግዚአብሔርን የኪዳኑን ታቦት አምጥተው የቤተ መቅደሱ ውስጠኛ ክፍል ወደ ቅድስተ ቅዱሳኑ አግብተው ከኪሩቤል ክንፍ በታች ባለው ስፍራው አኖሩት።
መሎጊያዎቹ በጣም ከመርዘማቸው የተነሣ ጫፎቻቸው ከቅድስተ ቅዱሳኑ ፊት ለፊት ካለው ከቅድስት ይታዩ ነበር፤ ከቅድስት ወዲያ ላለ ሰው ግን አይታዩም ነበር፤ እስከ ዛሬም ድረስ እዚያው ይገኛሉ።
“ከዚህም በላይ የቡሖአችንን፣ የእህል ቍርባናችንን፣ የዛፎቻችንን ፍሬ ሁሉ፣ አዲሱን የወይን ጠጃችንንና የዘይታችንን በኵራት ወደ ካህናቱ፣ ወደ አምላካችን ቤት ዕቃ ቤቶች እናመጣለን። እኛ በምንሠራባቸው ከተሞች ሁሉ ያለውን ዐሥራት የሚሰበስቡት ሌዋውያን ስለ ሆኑ፣ የሰብላችንን ዐሥራት ወደ ሌዋውያኑ እናመጣለን።
በዚያ ቀን ስጦታው፣ በኵራቱና ዐሥራቱ የሚቀመጥበትን ዕቃ ቤት የሚጠብቁ ሰዎች ተሾሙ። እነርሱም በየከተሞች ዙሪያ ከሚገኙት የዕርሻ ቦታዎች ሕጉ በሚያዝዘው መሠረት የካህናቱንና የሌዋውያኑን ድርሻ ወደ ዕቃ ቤቱ ማምጣት ነበረባቸው፤ ይሁዳ በሚያገለግሉ ካህናትና ሌዋውያን ደስ ተሠኝተው ነበርና።
ለርዳታ በጮኽሁ ጊዜ፣ ወደ ቅዱስ ማደሪያህ፣ እጆቼን በዘረጋሁ ጊዜ፣ የልመናዬን ቃል ስማ።
በምስክሩ ታቦት ላይ ባሉት በሁለቱ ኪሩቤል መካከል፣ በስርየት መክደኛው ላይ በዚያ እኔ ከአንተ ጋራ እገናኛለሁ፤ ለእስራኤላውያን የሚሆኑትን ትእዛዞቼንም እሰጥሃለሁ።
ይዘኸኝ ሂድ፤ እንፍጠን! ንጉሡ ወደ ዕልፍኞቹ አምጥቶኛል። በአንተ ደስ ይለናል፤ ሐሤትም እናደርጋለን፤ ከወይን ጠጅ ይልቅ ፍቅርህን እንወድሳለን። አንተን እንደዚህ ማፍቀራቸው ትክክል ነው።
“ወደ ሬካባውያን ሄደህ ወደ እግዚአብሔር ቤት አምጣቸው፤ ወደ አንዱም ክፍል አስገብተህ የሚጠጡትን ወይን ጠጅ ስጣቸው።”
ወደ እግዚአብሔር ቤት አመጣኋቸው፤ ወደ ሐናን ልጆች ክፍልም አስገባኋቸው፤ የሐናን አባት ጌዴልያም የእግዚአብሔር ሰው ነበረ። ክፍሉም በመኳንንቱ ክፍል አጠገብ፣ ከመዕሤያ ክፍል በላይ ነበር፤ መዕሤያም የበር ጠባቂው የሰሎም ልጅ ነበረ፤
ከዚያም ወደ ውጩ አደባባይ አመጣኝ፤ እዚያም በአደባባዩ ዙሪያ የተሠሩ ክፍሎችና ድንጋይ የተነጠፈበት መመላለሻ አየሁ፤ በመመላለሻውም ዙሪያ ሠላሳ ክፍሎች ነበሩ።
በውስጠኛው አደባባይ፣ ከውስጠኛው በር ውጭ፣ ሁለት ክፍሎች ነበሩ፤ አንዱ በደቡብ ትይዩ በሰሜን በር በኩል ሲሆን፣ ሌላው በሰሜን ትይዩ በደቡብ በር በኩል ነበር።
እርሱም የውስጠኛውን መቅደስ ርዝመት ለካ፤ ሃያ ክንድ ነበር፤ ወርዱም የውጪውን ግድግዳ ጨምሮ ሃያ ክንድ ነበር፤ እርሱም፣ “ይህ ቅድስተ ቅዱሳን ነው” አለኝ።
እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “እኔ በስርየቱ መክደኛ ላይ በደመና ውስጥ እገለጣለሁና ወንድምህ አሮን በመጋረጃው ውስጥ ወዳለው ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ማለት በታቦቱ ላይ ወዳለው ወደ ስርየቱ መክደኛ ፊት፣ በፈለገ ጊዜ ሁሉ እንዳይገባና እንዳይሞት ንገረው።
ሙሴ ከእግዚአብሔር ጋራ ለመነጋገር ወደ መገናኛው ድንኳን በገባ ጊዜ ከምስክሩ ታቦት መክደኛ በላይ በሁለቱ ኪሩቤል መካከል ድምፅ ሲናገረው ሰማ፤ አነጋገረውም።