የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም በአራተኛው ዓመት ዚፍ በተባለው ወር መሠረቱ ተጣለ፤
እስራኤላውያን ከግብጽ በወጡ በአራት መቶ ሰማንያ ዓመት፣ ሰሎሞን በእስራኤል ላይ በነገሠ በአራተኛው ዓመት፣ ዚፍ በተባለው በሁለተኛው ወር ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ መሥራት ጀመረ።
በዐሥራ አንደኛው ዓመት ቡል በተባለውም በስምንተኛው ወር ቤተ መቅደሱ በዝርዝር ጥናቱ መሠረት እንደ ታቀደው ተፈጸመ፤ ሠርቶ የጨረሰውም በሰባት ዓመት ጊዜ ውስጥ ነበር።
ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስና ቤተ መንግሥቱን ሠርቶ ከጨረሰና ለመሥራት የፈለገውንም ሁሉ ካከናወነ በኋላ፣
ሰሎሞን ሁለቱን ሕንጻዎች፣ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስና የንጉሡን ቤተ መንግሥት ሠርቶ በፈጸመበት በሃያኛው ዓመት መጨረሻ፣
በነገሠም በአራተኛው ዓመት፣ በሁለተኛው ወር፣ በሁለተኛው ቀን ቤተ መቅደሱን መሥራት ጀመረ።
የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ መሠረት ከተጣለበት ዕለት አንሥቶ እስከ ፍጻሜው ድረስ ያለው የሰሎሞን ሥራ ሁሉ ተከናወነለት፤ በዚሁ ሁኔታም የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ሥራ ከፍጻሜ ደረሰ።