“ስለምትሠራው ስለዚህ ቤተ መቅደስ ሥርዐቴን ብትከተል፣ ፍርዴን በተግባር ብትገልጸው፣ ትእዛዞቼን ብትጠብቅና ብትመላለስባቸው ለአባትህ ለዳዊት የሰጠሁትን ተስፋ በአንተ እፈጽመዋለሁ፤
“ሂድና ባሪያዬን ዳዊትን፣ ‘እንዲህ ብለህ ንገረው፤ እግዚአብሔር የሚለው ይህን ነው፤ የምኖርበትን ቤት የምትሠራልኝ አንተ ነህን? በለው።
ምንም እንኳ ሌሎች አማልክትን እንዳይከተል ሰሎሞንን ቢከለክለውም፣ ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ትእዛዝ አልጠበቀም፤
አባትህ ዳዊት እንዳደረገው በመንገዴ ብትሄድ፣ ሥርዐቴንና ትእዛዜን ብትጠብቅ ዕድሜህን አረዝመዋለሁ።”
የእግዚአብሔርም ቃል እንዲህ ሲል ወደ ሰሎሞን መጣ፤
“አሁንም የእስራኤል አምላክ እግዚአብሔር ሆይ፤ ለባሪያህ ለአባቴ ለዳዊት፣ ‘ልጆችህ አንተ እንደ አደረግኸው ሁሉ በሚያደርጉት ሁሉ በጥንቃቄ በፊቴ ቢመላለሱ፣ በእስራኤል ዙፋን ላይ በፊቴ የሚቀመጥ ሰው ፈጽሞ አታጣም’ ብለህ የሰጠኸውን ተስፋ አጽናለት።
ለስሜ ቤት የሚሠራልኝ እርሱ ነው። እርሱ ልጅ ይሆነኛል፤ እኔም አባት እሆነዋለሁ። ዙፋኑንም በእስራኤል ላይ ለዘላለም አጸናለሁ።’
“አንተም ልጄ ሰሎሞን ሆይ፤ እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ስለሚመረምርና ሐሳብን ሁሉ ስለሚያውቅ፣ የአባትህን አምላክ ዕወቅ፤ በፍጹም ልብና በበጎ ፈቃድ አገልግለው። ከፈለግኸው ታገኘዋለህ፤ ከተውኸው ግን እርሱም ለዘላለም ይተውሃል።
ወንዶች ልጆችህ ኪዳኔን፣ የማስተምራቸውንም ምስክርነቴን ቢጠብቁ፣ ልጆቻቸው በዙፋንህ ላይ፣ ለዘላለም ይቀመጣሉ።”
መንገዳችሁንና ሥራችሁን በርግጥ ብታሳምሩ፣ በመካከላችሁ ቅንነት ቢኖር፣
“የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘በመንገዴ ብትሄድ፣ ትእዛዜንም ብትጠብቅ፣ ቤቴን ታስተዳድራለህ፤ በአደባባዮቼም ላይ ኀላፊ ትሆናለህ፤ በዚህ በቆሙት መካከል ቦታ እሰጥሃለሁ።
ይህም የሚሆነው በእምነታችሁ ተመሥርታችሁና ተደላድላችሁ በመቆም ከሰማችሁት የወንጌል ተስፋ ሳትናወጡ ጸንታችሁ ብትኖሩ ነው። እናንተ የሰማችሁትና ከሰማይ በታች ላለ ፍጥረት ሁሉ የተሰበከውም ወንጌል ይኸው ነው፤ እኔም ጳውሎስ ለዚህ ወንጌል አገልጋይ ሆንሁ።