ንጉሥ ሰሎሞን ከመላው እስራኤል የጕልበት ሠራተኞችን መለመለ፤ ቍጥራቸውም ሠላሳ ሺሕ ነበር።
አሒሳር፣ የቤተ መንግሥቱ አዛዥ፤ የዓብዳ ልጅ አዶኒራም የግዳጅ ሥራ ተቈጣጣሪ።
ንጉሥ ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ፣ የራሱን ቤተ መንግሥት፣ ሚሎን፣ የኢየሩሳሌምን ቅጥር፣ አሦርን፣ መጊዶንና ጌዝርን ለመሥራት የጕልበት ሠራተኞች መልምሎ ነበር።
“አባትህ ቀንበራችንን አከበደብን፤ አንተ ግን አስጨናቂውን ሥራና በላያችን የጫነብንን ከባድ ቀንበር አቅልልልን፤ እኛም እንገዛልሃለን።”
እስራኤላውያን ያላጠፏቸውን፣ በምድሪቱ የቀሩትን የእነዚህን ሕዝቦች ዘሮች እስከ ዛሬ ድረስ እንደሚደረገው የጕልበት ሥራ ይሠሩ ዘንድ ሰሎሞን መለመላቸው፤