የዮዳሄ ልጅ በናያስ፣ የሰራዊቱ ዋና አዛዥ፤ ሳዶቅና አብያታር፣ ካህናት፤
ሱሳ ጸሓፊ፣ ሳዶቅና አብያታር ካህናት ነበሩ፤
የዮዳሄ ልጅ በናያስ የከሊታውያንና የፈሊታውያን አዛዥ ነበር፤ የዳዊት ወንዶች ልጆች ደግሞ አማካሪዎች ነበሩ።
ንጉሡም በኢዮአብ ቦታ የዮዳሄን ልጅ በናያስን በሰራዊቱ ላይ ሾመ፤ በአብያታርም ቦታ ካህኑን ሳዶቅን ተካ።