የዒዶ ልጅ አሒናዳብ፤ በመሃናይም፣
ያዕቆብም ባያቸው ጊዜ፣ “ይህ የእግዚአብሔር ሰፈር ነው” አለ፤ የዚያንም ቦታ ስም መሃናይም አለው።
አቤሴሎም ከመላው የእስራኤል ሰዎች ጋራ ዮርዳኖስን ሲሻገር፣ ዳዊት ግን መሃናይም ደርሶ ነበር።
ዳዊት መሃናይም ሲደርስ፣ ከአሞናውያን ከተማ ከረባት የመጣው፣ የናዖስ ልጅ ሾቢ፣ ከሎደባር የመጣው የዓሚኤል ልጅ ማኪርና ከሮግሊም የመጣው ገለዓዳዊው ቤርዜሊ
በዚህ ጊዜ የሳኦል ሰራዊት አዛዥ የኔር ልጅ አበኔር፣ የሳኦልን ልጅ ኢያቡስቴን ወስዶ ወደ መሃናይም አሻገረው፤
በገለዓድ ባለው የምናሴ ነገድ እኩሌታ ላይ የተሾመው፣ የዘካርያስ ልጅ አዶ፤ በብንያም ነገድ ላይ የተሾመው፣ የአበኔር ልጅ የዕሢኤል።
ከሐሴቦን እስከ ራማት ምጽጳና ከዚያም እስከ ብጦኒም፣ ከመሃናይም እስከ ደቤር ግዛት ያለውን፣
ከጋድ ነገድ፣ በገለዓድ ውስጥ ለነፍሰ ገዳይ መማፀኛ የሆነችው ከተማ ራሞት መሃናይም፣