“የዚህች ሴት ሕፃን ልጅ ስለ ተኛችበት ሌሊት ሞተ።
እኔ ከወለድሁ ከሦስት ቀን በኋላም፣ ይህች ሴት ወለደች፤ የነበርነው እኛ ብቻ ነን፤ ከሁለታችን በቀር በዚያ ቤት ማንም አልነበረም።
ስለዚህም በእኩለ ሌሊት ተነሥታ፣ እኔ አገልጋይህ ተኝቼ ሳለሁ ልጄን ከአጠገቤ ወሰደችው፤ ከዚያም የእኔን ልጅ ራሷ ታቅፋ፣ የሞተ ልጇን አምጥታ በዕቅፌ አደረገችው።