Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



1 ነገሥት 3:16

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በዚህ ጊዜ ሁለት ዝሙት ዐዳሪዎች ወደ ንጉሡ መጥተው ከፊቱ ቆሙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሰሎሞንም ከእንቅልፉ ነቃ፤ እነሆ ሕልም መሆኑን ተረዳ። ከዚያም ወደ ኢየሩሳሌም ተመልሶ፣ በጌታ ኪዳን ታቦት ፊት ቆመ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት አቀረበ፤ ለሹማምቱም ሁሉ ግብዣ አደረገ።

ከእነርሱም አንዲቱ እንዲህ አለች፣ “ጌታዬ ሆይ፤ ይህች ሴትና እኔ በአንድ ቤት ዐብረን እንኖራለን፤ ዐብራኝ እያለችም እኔ ልጅ ወለድሁ፤

በማግስቱም ሙሴ ሕዝቡን ለመዳኘት ተቀመጠ፤ እነርሱም በዙሪያው ከጧት እስከ ማታ ድረስ ቆሙ።

ክርክር በኖራቸው ቍጥር ጕዳያቸው ወደ እኔ ይመጣል፤ ለግራና ለቀኙ የሚሆነውን እኔ ወስኜ የእግዚአብሔርን ሥርዐትና ሕጎች እነግራቸዋለሁ።”

ነገርን መሰወር ለእግዚአብሔር ክብሩ ነው፤ ነገርን ፈልፍሎ ማውጣት ግን ለነገሥታት ክብራቸው ነው።

“ ‘ምድሪቱ ወደ ግልሙትና አዘንብላ በርኩሰት እንዳትሞላ፣ ሴት ልጅህ ጋለሞታ ትሆን ዘንድ አታዋርዳት።

ወደ መገናኛው ድንኳን መግቢያ ቀረቡ፤ በሙሴ፣ በካህኑ በአልዓዛር፣ በመሪዎችና በመላው ማኅበርም ፊት ቆመው እንዲህ አሉ፤

ወንድ ወይም ሴት እስራኤላዊ የቤተ ጣዖት አመንዝራ አይሁን።

ከዚያም የነዌ ልጅ ኢያሱ፣ “ሄዳችሁ ምድሪቱን፣ በተለይም የኢያሪኮን ከተማ ሰልሉ” ብሎ ከሰጢም ሁለት ሰላዮች በስውር ላከ፤ ሰዎቹም ሄደው ረዓብ ከተባለች ጋለሞታ ቤት ገቡ፤ በዚያም ዐደሩ።

ገለዓዳዊው ዮፍታሔ ኀያል ጦረኛ ነበረ፤ አባቱ ገለዓድ ነበር፤ እናቱም ጋለሞታ ነበረች።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች