ኢዮሣፍጥ ከአባቶቹ ጋራ አንቀላፋ፤ እነርሱ በተቀበሩበት በአባቱ በዳዊት ከተማ ተቀበረ። ልጁ ኢዮራምም በምትኩ ነገሠ።
ከዚያም ሰሎሞን ከአባቶቹ ጋራ አንቀላፋ፤ በአባቱ በዳዊት ከተማ ተቀበረ፤ ልጁም ሮብዓም በርሱ ፈንታ ነገሠ።
ሮብዓምም ከአባቶቹ ጋራ አንቀላፋ፤ እነርሱ በተቀበሩበትም በዳዊት ከተማ ተቀበረ። እናቱ ናዓማ የተባለች አሞናዊት ነበረች። ልጁ አብያም በርሱ ፈንታ ነገሠ።
አሳ ከአባቶቹ ጋራ አንቀላፋ፤ እነርሱ በተቀበሩበትም በአባቱ በዳዊት ከተማ ተቀበረ፤ ልጁ ኢዮሣፍጥም በርሱ ፈንታ ነገሠ።
ከዚያም ዳዊት ከአባቶቹ ጋራ አንቀላፋ፤ በዳዊትም ከተማ ተቀበረ።
አክዓብም ከአባቶቹ ጋራ አንቀላፋ፤ ልጁ አካዝያስም በእግሩ ተተክቶ ነገሠ።
በዚያ ጊዜም የአክዓብ ልጅ አካዝያስ ኢዮሣፍጥን “ሰዎቼ ከሰዎችህ ጋራ በመርከብ ይሂዱ” ሲል ጠይቆት ነበር፤ ኢዮሣፍጥ ግን ዕሺ አላለውም።
ኢዮሣፍጥ ከአባቶቹ ጋራ አንቀላፋ፤ እነርሱ በተቀበሩበትም በዳዊት ከተማ ተቀበረ። ልጁ ኢዮራምም በምትኩ ነገሠ።