Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



1 ነገሥት 21:19

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እንዲህም በለው፤ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ሰውየውን ገደልኸው፤ ደግሞ ርስቱን ልትወስድ?’ ከዚያም እንዲህ በለው፤ ‘እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ውሾች የናቡቴን ደም በላሱበት ቦታ የአንተንም ደም ውሾች እንዲሁ ይልሱታል!’ ”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

23 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግዚአብሔርም፣ “ዕራቍትህን መሆንህን ማን ነገረህ? ‘ከርሱ እንዳትበላ’ ብዬ ካዘዝሁህ ዛፍ በላህን?” አለው።

“እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘እነሆ ከራስህ ቤት ክፉ ነገር አስነሣብሃለሁ፤ ዐይንህ እያየም ሚስቶችህን ወስጄ ለአንተ ቅርብ ለሆነ ሰው ለአንዱ እሰጣለሁ፤ እርሱም በቀን ብርሃን ከሚስቶችህ ጋራ ይተኛል።

ታዲያ በፊቱ ክፉ ነገር በማድረግ፣ የእግዚአብሔርን ቃል ያቃለልኸው ስለ ምንድን ነው? ኬጢያዊውን ኦርዮን በሰይፍ መታህ፤ ሚስት እንድትሆንህም ሚስቱን ወሰድሃት፤ እርሱንም በአሞናውያን ሰይፍ ገደልኸው።

ሠረገላውንም አመንዝሮች በታጠቡበት በሰማርያ ኵሬ ዐጠቡት፤ እግዚአብሔርም እንደ ተናገረው ቃል ደሙን ውሾች ላሱት።

እንግዲህ እግዚአብሔር በአክዓብ ቤት ላይ ከተናገረው ቃል አንዲቱ እንኳ በምድር ላይ ወድቃ እንደማትቀር ዕወቁ። እግዚአብሔር በባሪያው በኤልያስ የተናገረውን ፈጽሟል።”

ደብዳቤውም በደረሳቸው ጊዜ፣ ሰዎቹ ሰባውን ልዑላን በሙሉ ወስደው ገደሏቸው። ራሳቸውንም በቅርጫት አድርገው ኢዩ ዘንድ ወደ ኢይዝራኤል ላኩ።

በዚህ ጊዜ ኤልሳዕ በቤቱ ተቀምጦ ነበር፤ ሽማግሌዎችም ዐብረውት ተቀምጠው ነበር። ንጉሡም መልእክተኛ ቀድሞት እንዲሄድ አደረገ። የተላከውም ሰው ከመድረሱ በፊት ኤልሳዕ ለሽማግሌዎቹ፣ “ይህ ነፍሰ ገዳይ ራሴን ለመቍረጥ ሰው መላኩን ታያላችሁ? እነሆ፤ አሁንም መልእክተኛው ሲደርስ በሩን ዘግታችሁ እንዳይገባ አድርጉ። የጌታው የእግሩ ኮቴ ከኋላው ይሰማ የለምን?” አላቸው።

ስለዚህ ለመርዶክዮስ ባዘጋጀው ግንድ ላይ ሐማን ሰቀሉት፤ ከዚያም የንጉሡ ቍጣ በረደ።

ፍሬዋን ያለ ዋጋ በልቼ፣ የባለመሬቶቿን ነፍስ አሳዝኜ ከሆነ፣

እግርህ በጠላትህ ደም ውስጥ እንዲጠልቅ፣ የውሻህም ምላስ ከጠላትህ ድርሻውን እንዲያገኝ ነው።”

እግዚአብሔር ሆይ፤ ጠላቶቼ የሚያደርሱብኝን መከራ ተመልከት፤ አይተህም ራራልኝ፤ ከሞት ደጅም አንሥተህ መልሰኝ፤

እግዚአብሔር በትክክለኛ ፍርዱ የታወቀ ነው፤ ክፉዎችም በእጃቸው ሥራ ተጠመዱ። ሒጋዮን ሴላ

ነቢዩ ኤርምያስ ይህን ሁሉ ለይሁዳ ንጉሥ ለሴዴቅያስ በኢየሩሳሌም ነገረው፤

ገዥው ከንብረታቸው በማፈናቀል፤ የትኛውንም የሕዝቡን ርስት መውሰድ አይገባውም፤ ለወንድ ልጆቹ ርስት መስጠት ያለበት ከራሱ ንብረት ነው፤ ይኸውም ከሕዝቤ ማንም ከርስቱ እንዳይነቀል ነው።’ ”

“ከተማን ደም በማፍሰስ ለሚሠራ፣ በወንጀልም ለሚመሠርታት ወዮለት!

“በተጭበረበረ ትርፍ መኖሪያውን ለሚገነባ፣ ከጠላት እጅ ለማምለጥ፣ ቤቱን በከፍታ ላይ ለሚሠራ ወዮለት!

በምትፈርዱበትም ፍርድ ይፈረድባችኋል፤ በምትሰፍሩበትም መስፈሪያ ይሰፈርላችኋል።

ከዚያም አዶኒቤዜቅ፣ “የእጃቸውና የእግራቸው አውራ ጣቶች የተቈረጡባቸው ሰባ ነገሥታት ከገበታዬ ሥር የወደቀ ፍርፋሪ ይለቃቅሙ ነበር፤ አሁን ግን እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ የፈጸምሁትን አመጣብኝ” አለ፤ እነርሱም ወደ ኢየሩሳሌም አመጡት፤ በዚያም ሞተ።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች