Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



1 ነገሥት 20:39

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ንጉሡ በዚያ በሚያልፍበትም ጊዜ፣ ነቢዩ ጠርቶት እንዲህ አለው፤ “እኔ አገልጋይህ በተፋፋመው ጦርነት መካከል ገብቼ ሳለሁ፣ አንድ ሰው ምርኮኛ ይዞ መጥቶ ‘ይህን ሰው ጠብቅ፤ ቢያመልጥ በገመዱ ትገባለህ ወይም አንድ መክሊት ብር ትከፍላለህ’ አለኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

‘ታዲያ እኔ አገልጋይህ ሥራ በዝቶብኝ ወዲያ ወዲህ ስል ሰውየው አምልጦ ሄደ።’ ” የእስራኤልም ንጉሥ፣ “ራስህ ፈርደሃል፤ ይኸው ይፈጸምብሃል” አለው።

ነቢዩም ንጉሡን አለው፤ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘እኔ ፈጽሞ ይገደል ያልሁትን ሰው ለቅቀኸዋልና በገመዱ ትገባለህ፤ በሕዝቡም ፈንታ ያንተ ሕዝብ በገመዱ ይገባል።’ ”

ከዚያም የሚቃጠል መሥዋዕትና ሌላም መሥዋዕት ለማቅረብ ገቡ። በዚህ ጊዜም ኢዩ፣ “በእጃችሁ አሳልፌ ከሰጠኋችሁ ሰዎች አንድ እንኳ እንዲያመልጥ ያደረገ በገመዱ ይገባበታል” ብሎ በማስጠንቀቅ ውጭ ሰማንያ ሰዎች አዘጋጅቶ ነበር።

ባለጠግነት እንዳያታልልህ፣ የእጅ መንሻ ብዛትም እንዳያስትህ ተጠንቀቅ።

የሌላውን ሕይወት መቤዠት የሚችል ሰው፣ ወይም ለእግዚአብሔር ወጆ የሚከፍልለት ማንም የለም።

ሆኖም ካሳ እንዲከፍል ከተጠየቀ፣ የተጠየቀውን ሁሉ በመክፈል ሕይወቱን ይዋጅ።

የሰው ሀብቱ ለሕይወቱ ቤዛ ሊሆነው ይችላል፤ ድኻው ግን ሥጋት የለበትም።

ምንም ዐይነት ካሳ አይቀበልም፤ የቱንም ያህል ብዙ ቢሆን መማለጃን ዕሺ አይልም።

“የእግዚአብሔርን ሥራ በቸልታ የሚያከናውን ርጉም ይሁን፤ ሰይፉን ደም ከማፍሰስ የሚከላከል የተረገመ ይሁን!




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች