ከዚያም፣ “የምነግርሽ ጕዳይ አለኝ” አላት። እርሷም፣ “ዕሺ ተናገር” ብላ መለሰች።
ከዚያም ሴቲቱ፣ “እኔ አገልጋይህ ለጌታዬ ለንጉሡ አንዲት ቃል እንድናገር ፍቀድልኝ” አለችው። እርሱም፣ “ዕሺ ተናገሪ” አላት።
በዚህ ጊዜ የአጊት ልጅ አዶንያስ ወደ ሰሎሞን እናት ወደ ቤርሳቤህ ሄደ። ቤርሳቤህም፣ “የመጣኸው በሰላም ነውን?” ስትል ጠየቀችው። እርሱም፣ “አዎን በሰላም ነው” ብሎ መለሰ።
እርሱም፣ “መንግሥቱ የእኔ እንደ ነበረና እስራኤልም ሁሉ እኔ እንድነግሥ ዐይናቸውን ጥለውብኝ እንደ ነበር አንቺ ራስሽ ታውቂአለሽ፤ ሆኖም ነገሩ ከእግዚአብሔር የተቈረጠለት ሆነና ሁኔታዎች ተለዋውጠው፣ መንግሥቱ ለወንድሜ ተላለፈ።
ኢየሱስም፣ “ስምዖን ሆይ፤ የምነግርህ ነገር አለኝ” አለው። እርሱም፣ “መምህር ሆይ፤ ንገረኝ” አለው።