በድንጋዮቹም ለእግዚአብሔር ስም መሠዊያ ሠራ፤ በመሠዊያውም ዙሪያ ዐሥራ ዐምስት ሊትር ውሃ የሚይዝ ጕድጓድ ቈፈረ፤
እግዚአብሔርም ለአብራም ተገልጦ፣ “ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ” አለው። እርሱም ለተገለጠለት ለእግዚአብሔር በዚያ ስፍራ መሠዊያ ሠራ።
ዕንጨቱን ረበረበ፤ የወይፈኑንም ሥጋ በየብልቱ ከቈረጠ በኋላ፣ በዕንጨቱ ላይ አኖረው። ከዚያም፣ “ውሃ በአራት ጋን ሞልታችሁ፣ በመሥዋዕቱና በዕንጨቱ ላይ አፍስሱ” አላቸው።
ውሃውም በመሠዊያው ዙሪያ ፈሰሰ፤ ጕድጓዱንም ሞላው።
እንግዲህ ስትበሉም ሆነ ስትጠጡ፣ ወይም ማንኛውንም ነገር ስታደርጉ፣ ሁሉንም ነገር ለእግዚአብሔር ክብር አድርጉት።
በርሱ በኩል ለእግዚአብሔር አብ ምስጋና እያቀረባችሁ፣ በቃልም ሆነ በተግባር የምታደርጉትን ሁሉ በጌታ በኢየሱስ ስም አድርጉት።
በማግስቱም ጧት ሕዝቡ መሠዊያ ሠሩ፤ የሚቃጠል መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት አቀረቡ።
ጌዴዎንም በዚያ ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ፤ ስሙንም “እግዚአብሔር ሰላም ነው” ብሎ ጠራው፤ ይህ መሠዊያ የአቢዔዝራውያን ይዞታ በሆነው በዖፍራ ዛሬም ቆሞ ይታያል።
በዚህ ፍርስራሽ ጕብታ ላይ ለአምላክህ ለእግዚአብሔር የሚገባውን መሠዊያ ሥራ። ሰባብረህ በጣልኸው የአሼራ ምስል ዐምድ ሁለተኛውን ወይፈን ወስደህ የሚቃጠል መሥዋዕት አድርገህ አቅርበው።”
ከዚያም በአርማቴም ወዳለው ቤቱ ይመለስ ነበር፤ በዚያም ደግሞ በእስራኤል ላይ ይፈርድ ነበር። በዚያም ለእግዚአብሔር መሠዊያ ሠራ።
ሳሙኤልም አንድ የሚጠባ የበግ ግልገል ወስዶ ሙሉ ለሙሉ የሚቃጠል መሥዋዕት በማድረግ ለእግዚአብሔር አቀረበው፤ ስለ እስራኤልም ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ እግዚአብሔርም መለሰለት።