Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



1 ነገሥት 18:19

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አሁንም ሕዝቡ በቀርሜሎስ ተራራ እንዲገናኘኝ ለመላው እስራኤል ጥሪ አድርግ። ከኤልዛቤል ማእድ የሚቀለቡትን አራት መቶ ዐምሳውን የበኣል ነቢያት፣ አራት መቶውንም የአሼራ ነቢያት አምጣቸው።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

23 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አሳም ለአስጸያፊዋ የአሼራ ጣዖት ዐምድ በማቆሟ፣ አያቱን መዓካን ከእቴጌነቷ ሻራት፤ ጣዖቷንም በቄድሮን ሸለቆ አቃጠለው።

ደግሞም አክዓብ የአሼራን ምስል ዐምድ በማቆም ከርሱ በፊት ከነበሩት የእስራኤል ነገሥታት ይልቅ የእስራኤልን አምላክ እግዚአብሔርን ለቍጣ የሚያነሣሣ ድርጊት ፈጸመ።

ስለዚህ አክዓብ በመላው እስራኤል ጥሪ አደረገ፣ ነቢያቱንም በቀርሜሎስ ተራራ ሰበሰበ።

ከዚያም ኤልያስ እንዲህ አላቸው፤ “ከእግዚአብሔር ነቢያት የተረፍሁ እኔ ብቻ ነኝ፤ በኣል ግን አራት መቶ ዐምሳ ነቢያት አሉት።

ስለዚህ የእስራኤል ንጉሥ አራት መቶ ነቢያትን በአንድነት ሰብስቦ፣ “በገለዓድ በምትገኘው ራሞት ላይ ልዝመት ወይስ ልቅር?” ሲል ጠየቃቸው። እነርሱም፣ “እግዚአብሔር በንጉሡ እጅ አሳልፎ ይሰጣታልና ዝመትባት” አሉት።

አሁንም የበኣልን ነቢያት ሁሉ አገልጋዮቹንና ካህናቱንም በሙሉ ጥሩልኝ። ለበኣል ትልቅ መሥዋዕት ስለማቀርብ አንድ ሰው እንኳ እንዳይቀር። የማይመጣ ሰው ቢኖር ግን በሕይወት አይኖርም” ኢዩ ግን ይህን ማድረጉ የበኣልን አገልጋዮች ለማጥፋት ተንኰል መፍጠሩ ነበር።

ይሁን እንጂ እስራኤልን ከአሳተው ከኢዮርብዓም ቤት ኀጢአት አልተመለሱም፤ በዚያው ገፉበት እንጂ። የአሼራም ምስል ዐምድ በሰማርያ መመለኩ ቀጠለ።

እርሱም ወደ ቀርሜሎስ ተራራ ሄደ፤ ከዚያም ወደ ሰማርያ ተመለሰ።

ኤልሳዕም የእስራኤልን ንጉሥ፤ “ከአንተ ጋራ ምን የሚያገናኘን ጕዳይ አለና መጣህ፤ አሁን የአባትህና የእናትህ ነቢያት ወዳሉበት ሂድ” አለው። የእስራኤልም ንጉሥ መልሶ፣ “ይህማ አይሆንም፤ በሞዓብ እጅ አሳልፎ ሊሰጠን እኛን ሦስት ነገሥታት አንድ ላይ የጠራን እግዚአብሔር ነው” አለ።

ኢዮራምም ኢዩን ገና ሲያየው፣ “ኢዩ፣ የመጣኸው በሰላም ነውን?” ሲል ጠየቀው። ኢዩም፣ “የእናትህ የኤልዛቤል የጣዖት አምልኮና መተት እንዲህ በዝቶ እያለ ምን ሰላም አለ!” ሲል መለሰ።

ከዚህም በላይ በዙሪያችን ካሉት፣ ወደ እኛ ከሚመጡት አሕዛብ ሌላ አንድ መቶ ዐምሳ አይሁድና ሹማምት ከማእዴ ይካፈሉ ነበር።

እንዴት ውብ ነሽ! እንዴትስ ደስ የምትይ ነሽ! ፍቅሬ ሆይ፤ የምታስደስቺ ነሽ።

“በሰማርያ ባሉ ነቢያት ላይ፣ ደስ የማያሰኝ ነገር አይቻለሁ፤ በበኣል ስም ትንቢት ተናገሩ፤ ሕዝቤን እስራኤልን አሳቱ።

ስሙ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሆነው ንጉሡ እንዲህ ይላል፤ “በሕያውነቴ እምላለሁ”። በተራሮች መካከል ያለውን የታቦር ተራራ የሚመስል፣ ባሕርም አጠገብ ያለውን የቀርሜሎስ ተራራ የሚመስል አንድ የሚመጣ አለ።

እርሱም እንዲህ አለ፤ “እግዚአብሔር ከጽዮን ድምፁን ከፍ አድርጎ ያሰማል፤ ከኢየሩሳሌምም ያንጐደጕዳል፤ የእረኞች ማሰማሪያዎች ደርቀዋል፤ የቀርሜሎስም ዐናት ጠውልጓል።”

በቀርሜሎስ ጫፍ ላይ ቢሸሸጉም፣ ዐድኜ፣ ፈልጌ ከዚያ አወርዳቸዋለሁ፤ እይዛቸዋለሁም። በጥልቅ ባሕር ውስጥ ከእኔ ቢሸሸጉም፣ በዚያ እባቡ እንዲነድፋቸው አዝዘዋለሁ።

አላሜሌክ፣ ዓምዓድ እንዲሁም ሚሽአል። ድንበሩ በስተ ምዕራብ ቀርሜሎስንና ሺሖርሊብናትን ይነካል፤

ነገር ግን ሐሰተኞች ነቢያት በሕዝቡ መካከል እንደ ነበሩ፣ እንዲሁም በእናንተ መካከል ሐሰተኞች መምህራን ይነሣሉ፤ እነርሱም የዋጃቸውን ጌታ እንኳ ክደው፣ ጥፋት የሚያስከትል የስሕተት ትምህርት በስውር ያስገባሉ፤ በዚህም በራሳቸው ላይ ድንገተኛ ጥፋት ያመጣሉ።

ነገር ግን አውሬው ተያዘ፤ ከርሱም ጋራ በፊቱ ምልክቶችን ያደርግ የነበረው ሐሰተኛው ነቢይ ተያዘ። በእነዚህ ምልክቶች የአውሬውን ምልክት የተቀበሉትንና ለምስሉ የሰገዱትን አሳተ። ሁለቱም በሕይወት እንዳሉ በዲን ወደሚቃጠለው የእሳት ባሕር ተጣሉ።

ይሁን እንጂ የምነቅፍብህ ነገር አለኝ፤ ነቢይ ነኝ የምትለዋን ሴት ኤልዛቤልን ችላ ብለሃታል፤ እርሷ ባሮቼ እንዲሴስኑና ለጣዖት የተሠዋ ምግብ እንዲበሉ በትምህርቷ ታስታቸዋለች።

ሳሙኤልም ጧት ተነሥቶ በማለዳ ሳኦልን ለመገናኘት ሄደ፤ ነገር ግን፣ “ሳኦል ወደ ቀርሜሎስ ሄዷል፤ ለራሱ ክብር የመታሰቢያ ሐውልት በዚያ ካቆመ በኋላ ተመልሶ ወደ ጌልገላ ወርዷል” ተብሎ ተነገረው።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች