አሳ ከአባቶቹ ጋራ አንቀላፋ፤ እነርሱ በተቀበሩበትም በአባቱ በዳዊት ከተማ ተቀበረ፤ ልጁ ኢዮሣፍጥም በርሱ ፈንታ ነገሠ።
ከዚያም ዳዊት ከአባቶቹ ጋራ አንቀላፋ፤ በዳዊትም ከተማ ተቀበረ።
በሦስተኛው ዓመት ግን የይሁዳ ንጉሥ ኢዮሣፍጥ የእስራኤልን ንጉሥ ለመጐብኘት ወረደ።
የሰሎሞን ልጅ ሮብዓም ነበረ፤ የሮብዓም ልጅ አብያ፣ የአብያ ልጅ አሳ፣ የአሳ ልጅ ኢዮሣፍጥ፣
በአሳ ዘመነ መንግሥት ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ የተከናወነው ሥራ በይሁዳና በእስራኤል ነገሥታት የታሪክ መጻሕፍት ተጽፏል።
አሳም በነገሠ በአርባ አንደኛው ዓመት ሞተ፤ ከአባቶቹ ጋራ አንቀላፋ።
አሣፍ ኢዮሣፍጥን ወለደ፤ ኢዮሣፍጥ ይሆራምን ወለደ፤ ይሆራም ዖዝያንን ወለደ፤