በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ሦስት ዓመት ገዛ፤ እናቱ መዓካ የተባለች የአቤሴሎም ልጅ ነበረች።
በኢየሩሳሌምም አርባ አንድ ዓመት ነገሠ፤ እናቱ መዓካ ትባላለች፤ እርሷም የአቤሴሎም ልጅ ነበረች።
አሳም ለአስጸያፊዋ የአሼራ ጣዖት ዐምድ በማቆሟ፣ አያቱን መዓካን ከእቴጌነቷ ሻራት፤ ጣዖቷንም በቄድሮን ሸለቆ አቃጠለው።
ኢዮሣፍጥ መንገሥ በጀመረ ጊዜ ዕድሜው ሠላሳ ዐምስት ዓመት ነበረ፤ በኢየሩሳሌም ተቀምጦ ሃያ ዐምስት ዓመት ገዛ። እናቱም የሺልሒ ልጅ ዓዙባ ነበረች።
ኢዮርብዓም በነገሠ በዐሥራ ስምንተኛው ዓመት፣ አብያ በይሁዳ ነገሠ።
በኢየሩሳሌም ተቀምጦም ሦስት ዓመት ገዛ። እናቱ ሚካያ ትባላለች፤ እርሷም የጊብዓ ተወላጅ የኡርኤል ልጅ ነበረች። በአብያና በኢዮርብዓምም መካከል ጦርነት ነበር።