ስለዚህ ነቢዩ፣ “ዐብረን ወደ ቤት እንሂድና ምግብ ብላ” አለው።
እየጋለበ ያን የእግዚአብሔር ሰው ተከተለው። ከዚያም በአንድ የወርካ ዛፍ ሥር ተቀምጦ አገኘውና፣ “ከይሁዳ የመጣኸው የእግዚአብሔር ሰው አንተ ነህን?” ሲል ጠየቀው። እርሱም፣ “አዎን እኔ ነኝ” ብሎ መለሰለት።
የእግዚአብሔርም ሰው እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “ተመልሼ ከአንተ ጋራ አልሄድም፤ በዚህ ቦታም ዐብሬህ እንጀራ አልበላም፤ ውሃም አልጠጣም፤