እንዲሁም ከጥፍጥፍ ወርቅ ሦስት መቶ ትንንሽ ጋሻዎችን አበጀ፤ በእያንዳንዱ ጋሻ የገባው ጥፍጥፍ ወርቅ ሦስት ምናን ነበር። ንጉሡም ጋሻዎቹን የሊባኖስ ደን በተባለው ቤተ መንግሥት ውስጥ አኖረ።
የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ንብረትና የቤተ መንግሥቱን ንብረት ዘርፎ ወሰደ፤ ሰሎሞን ያሠራው የወርቅ ጋሻ፤ ሰሎሞን ያሠራቸው የወርቅ ጋሻዎች ሁሉ እንኳ ሳይቀሩ ሁሉንም ነገር አጋዘ።
የሊባኖስ ዱር የተባለ ቤተ መንግሥት ሠራ፤ ይህም ርዝመቱ መቶ ክንድ፣ ወርዱ ዐምሳ ክንድ፣ ቁመቱ ሠላሳ ክንድ ሲሆን፣ በአራት ረድፍ የቆሙ የዝግባ ምሰሶዎች ደግፈው የያዟቸው አግዳሚ የዝግባ ተሸካሚዎች ነበሩት።
የግብጽ ንጉሥ ሺሻቅ ኢየሩሳሌምን በወረረ ጊዜ፣ የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ንብረትና የቤተ መንግሥቱን ንብረት ዘርፎ ወሰደ፤ ሰሎሞን ያሠራቸው የወርቅ ጋሻዎች እንኳ ሳይቀሩ፣ ሁሉንም ነገር አጋዘ።
የይሁዳን መከላከያዎች ገልጧል። በዚያ ቀን በዱር ግምጃ ቤት የነበረውን፣ የጦር መሣሪያ ተመለከትህ፤