ላገቡት ይህን ትእዛዝ እሰጣለሁ፤ ይህም ትእዛዝ የጌታ እንጂ የእኔ አይደለም። ሚስት ከባሏ አትለያይ፤
የእስራኤል ቤት ሆይ፤ ለባሏ ታማኝ እንዳልሆነች ሚስት፣ ስታታልሉኝ ኖራችኋል፤” ይላል እግዚአብሔር።
እኔ ግን እላችኋለሁ፤ ዝሙት ፈጽማ እስካልተገኘች ድረስ፣ ሚስቱን የሚፈታ ሁሉ እንድታመነዝር ያደርጋታል፤ በዚህ ሁኔታ የተፈታችውንም ሴት የሚያገባ ያመነዝራል።
አንዳንድ ፈሪሳውያንም መጥተው፣ “አንድ ባል ሚስቱን እንዲፈታ ተፈቅዷልን?” ብለው ሊፈትኑት ጠየቁት።
“ሚስቱን ፈትቶ ሌላዪቱን የሚያገባ ሁሉ ያመነዝራል፤ የተፈታችውንም ሴት የሚያገባ ያመነዝራል።”
ብትለያይ ግን ሳታገባ ትኑር፤ አለዚያ ከባሏ ጋራ ትታረቅ፤ ባልም ሚስቱን አይፍታት።
ለሌሎች ደግሞ እንዲህ እላለሁ፤ ይህንም የምለው እኔ እንጂ ጌታ አይደለም። ያላመነች ሚስት ያለው ወንድም ቢኖርና ሚስቱ ዐብራው ለመኖር የምትፈቅድ ከሆነ፣ ሊፈታት አይገባውም።
ነገር ግን የማያምነው ወገን መለየት ከፈለገ ይለይ፤ አንድ ወንድም ወይም እኅት በዚህ ሁኔታ የታሰሩ አይደሉም፤ እግዚአብሔር የጠራን በሰላም እንድንኖር ነው።
ስለ ደናግል፣ ከጌታ የተቀበልሁት ትእዛዝ የለኝም፤ ይሁን እንጂ፣ ከጌታ ምሕረት የተነሣ እንደ ታማኝ ሰው፣ ምክሬን እሰጣለሁ።
እንደ እኔ ከሆነ ግን ሳታገባ እንዲሁ ብትኖር ይበልጥ ደስተኛ ትሆናለች፤ እኔም ደግሞ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ያለ ይመስለኛል።
ይህን የምለው ግን እንደ ትእዛዝ ሳይሆን እንደ ምክር ነው።