እንደ እነርሱ ላሉትና ከእነርሱም ጋራ በአገልግሎት ለሚደክሙ ሁሉ ታዘዙ።
ከዚያም መንፈስ በሠላሳዎቹ አለቃ በዓማሣይ ላይ ወረደ፤ እርሱም እንዲህ አለ፤ “ዳዊት ሆይ፤ እኛ የአንተ ነን፤ የእሴይ ልጅ ሆይ፤ እኛ ከአንተ ጋራ ነን፤ ሰላም ፍጹም ሰላም ለአንተ ይሁን፤ አንተን ለሚረዱም ሁሉ ሰላም ይሁን፤ አምላክህ ይረዳሃልና።” ስለዚህ ዳዊት ተቀበላቸው፤ የሰራዊቱም አለቃ አደረጋቸው።
ከፀሓይ በታች ከሚለፋበት ተግባር ሁሉ፣ ሰው ምን ትርፍ ያገኛል?
በጌታ ሆነው በትጋት ለሚሠሩት ሴቶች፣ ለፕሮፊሞናና ለጢሮፊሞሳ ሰላምታ አቅርቡልኝ። በጌታ ሆና እጅግ ለደከመችው ለሌላዋ ሴት፣ ለተወደደችው ለጠርሲዳ ሰላምታ አቅርቡልኝ።
በክርስቶስ ኢየሱስ ዐብረውኝ ለሚያገለግሉት ለጵርስቅላና ለአቂላ ሰላምታ አቅርቡልኝ።
ለእናንተ ብዙ ለደከመችው ለማርያ ሰላምታ አቅርቡልኝ።
በክርስቶስ ዐብሮን ለሚሠራው ለኢሩባኖንና ለውድ ወዳጄ ለስንጣክን ሰላምታ አቅርቡልኝ።
እግዚአብሔር በቤተ ክርስቲያን ውስጥ አንደኛ ሐዋርያትን፣ ሁለተኛ ነቢያትን፣ ሦስተኛ መምህራንን፣ ቀጥሎም ታምራት አድራጊዎችን፣ የመፈወስ ስጦታዎች ያላቸውን፣ ሌሎችን የመርዳት ስጦታ ያላቸውን፣ የማስተዳደር ስጦታ ያላቸውንና በልዩ ልዩ ልሳን የመናገር ስጦታ ያላቸውን ሰዎች መድቧል።
እኛ የእግዚአብሔር የሆንን ዐብሮ ሠራተኞች ነንና፤ እናንተም የእግዚአብሔር ዕርሻ፣ የእግዚአብሔር ሕንጻ ናችሁ።
ለክርስቶስ ካላችሁ አክብሮታዊ ፍርሀት የተነሣ አንዳችሁ ለአንዳችሁ ተገዙ።
አዎን፤ አንተ ታማኝ ባልደረባዬ ሆይ፤ ወንጌልን በማሠራጨት ረገድ ከእኔና ከቀሌምንጦስ ጋራ እንዲሁም ስማቸው በሕይወት መጽሐፍ ከተጻፉት ከሌሎች የሥራ ጓደኞቼ ጋራ የተጋደሉትን እነዚህን ሴቶች እንድትረዳቸው እለምንሃለሁ።
ከእምነት የሆነውን ሥራችሁን፣ ከፍቅር የመነጨውን ድካማችሁንና በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ባላችሁ ተስፋ የተገኘውን ጽናታችሁን በአምላካችንና በአባታችን ፊት ዘወትር እናስባለን።
ወንድሞች ሆይ፤ ጥረታችንንና ድካማችንን ታስታውሳላችሁ፤ በማንም ላይ ሸክም እንዳንሆን ሌሊትና ቀን እየሠራን የእግዚአብሔርን ወንጌል ሰበክንላችሁ።
እንግዲህ ወንድሞች ሆይ፤ በእናንተ መካከል በትጋት የሚሠሩትን፣ በጌታም የበላዮቻችሁና መካሪዎቻችሁ የሆኑትን እንድታከብሯቸው እንለምናችኋለን፤
ቤተ ክርስቲያንን በሚገባ የሚያስተዳድሩ፣ ይልቁንም በመስበክና በማስተማር የሚተጉ ሽማግሌዎች ዕጥፍ ክብር ይገባቸዋል፤
ለመሪዎቻችሁ ታዘዙ፤ ተገዙላቸውም፤ ምክንያቱም እነርሱ በብርቱ የሚያስጠይቃቸው ነገር ስላለባቸው፣ ስለ ነፍሳችሁ ጕዳይ ይተጋሉ። ስለዚህ ሥራቸውን በሐዘን ሳይሆን በደስታ ማከናወን እንዲችሉ ታዘዟቸው፤ አለዚያ አይበጃችሁም።
ለመሪዎቻችሁ ሁሉና ለቅዱሳን ሁሉ ሰላምታ አቅርቡልኝ። ከኢጣሊያ የሆኑትም ሰላምታ ያቀርቡላችኋል።
እግዚአብሔር ዐመፀኛ አይደለም፤ እርሱ ሥራችሁን እንዲሁም በፊትም ሆነ አሁን ቅዱሳንን በመርዳት ስለ ስሙ ያሳያችሁትን ፍቅር አይረሳም።
ጕልማሶች ሆይ፤ እናንተም እንዲሁ ለሽማግሌዎች ተገዙ፤ ሁላችሁም እርስ በርስ በመከባበር ትሕትናን ልበሱ፤ ምክንያቱም፣ “እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል፤ ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል።”
እንግዲህ ዐብረን ለእውነት እንድንሠራ እንዲህ ያሉትን ሰዎች ልናስተናግድ ይገባናል።
ደግሞም በትዕግሥት መጽናትህንና ስለ ስሜም መከራ መቀበልህን ዐውቃለሁ፤ በዚህ ሁሉ አልታከትህም።