አካል የተሠራው ከብዙ ብልቶች እንጂ ከአንድ ብልት አይደለም።
አካል ብዙ ብልቶች ቢኖሩትም አንድ አካል ነው፤ ነገር ግን ብልቶች ብዙ ቢሆኑም አካል አንድ ነው። ክርስቶስም እንደዚሁ ነው።
እግር፣ “እኔ እጅ ስላልሆንሁ የአካል ክፍል አይደለሁም” ቢል ይህን በማለቱ የአካል ክፍል መሆኑ ይቀራልን?
ሁሉም አንድ ብልት ቢሆን ኖሮ አካል ከየት ይገኝ ነበር?
እንግዲህ ብልቶች ብዙ ናቸው፣ አካል ግን አንድ ነው።
ስለዚህ ውሸትን አስወግዳችሁ፣ እያንዳንዳችሁ ከባልንጀራችሁ ጋራ እውነትን ተነጋገሩ፤ ሁላችንም የአንድ አካል ብልቶች ነንና።