ወንድ ራሱን መከናነብ የለበትም፤ ወንድ የእግዚአብሔር ምሳሌና ክብር ነውና፤ ሴት ግን የወንድ ክብር ናት፤
ሴቲቱንም እንዲህ አላት፤ “በምጥ ጊዜ ጭንቅሽን አበዛለሁ፤ በሥቃይም ትወልጃለሽ፤ ፍላጎትሽም ወደ ባልሽ ይሆናል፤ እርሱም የበላይሽ ይሆናል።”
የተጻፈው የአዳም የትውልድ ሐረግ እንደሚከተለው ነው። እግዚአብሔር ሰውን ሲፈጥረው በራሱ አምሳል አበጀው፤
“የሰውን ደም የሚያፈስስ ሁሉ፣ ደሙ በሰው እጅ ይፈስሳል፤ በእግዚአብሔር አምሳል፣ እግዚአብሔር ሰውን ሠርቶታልና።
በእጆችህ ሥራ ላይ ሾምኸው፤ ሁሉንም ከእግሮቹ በታች አስገዛህለት፤
መልካም ሴት ለባሏ ዘውድ ናት፤ አሳፋሪ ሚስት ግን ዐጥንቱ ውስጥ እንዳለ ንቅዘት ናት።
ነገር ግን ይህን እንድታውቁ እወድዳለሁ፤ የወንድ ሁሉ ራስ ክርስቶስ ነው፤ የሴትም ራስ ወንድ ነው፤ የክርስቶስም ራስ እግዚአብሔር ነው።
ሴት ራሷን የማትሸፍን ከሆነ፣ ጠጕሯን ትቈረጥ፤ ጠጕሯን መቈረጥ ወይም መላጨት የሚያሳፍር መስሎ ከታያት ግን ራሷን ትሸፈን።
ስለ ቲቶ የሚጠይቅ ቢኖር፣ እርሱ እናንተን ለማገልገል ዐብሮኝ የሚሠራ ባልደረባዬ ነው፤ ስለ ወንድሞቻችንም የሚጠይቅ ቢኖር እነርሱ የአብያተ ክርስቲያናት ተወካዮችና የክርስቶስ ክብር ናቸው።
በምላሳችን ጌታንና አብን እንባርካለን፤ በርሷም በእግዚአብሔር አምሳል የተፈጠሩትን ሰዎች እንረግማለን።