Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



1 ዜና መዋዕል 9:13

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የቤተ ሰብ አለቃ የነበሩት ካህናት ቍጥር አንድ ሺሕ ሰባት መቶ ስድሳ ነበረ፤ እነዚህም በእግዚአብሔር ቤት ለሚከናወነው አገልግሎት ብቁ ሰዎች ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከኬብሮናውያን፤ ለሐሻብያ፣ ጠንካራና ጐበዝ የሆኑ አንድ ሺሕ ሰባት መቶ ሰዎች ከዮርዳኖስ በስተ ምዕራብ በሚገኘው የእስራኤል ምድር ላለው የእግዚአብሔር ሥራና ለንጉሡም አገልግሎት ኀላፊዎች ሆነው ተመደቡ።

ይሪያም ጠንካሮችና የቤተ ሰባቸው አለቆች የሆኑ ሁለት ሺሕ ሰባት መቶ ሥጋ ዘመዶች ነበሩት። ንጉሥ ዳዊትም እነዚህን የእግዚአብሔር ለሆነውና የንጉሡም በሆነው ጕዳይ ላይ ሮቤልን፣ ጋድንና የምናሴን ነገድ እኩሌታ ኀላፊ አድርጎ ሾማቸው።

እንዲሁም ልጁ ሸማያ ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ እነርሱም በቂ ችሎታ ስለ ነበራቸው የአባታቸው ቤት መሪዎች ሆነው ነበር።

የመልክያ ልጅ፣ የፋስኮር ልጅ፣ የይሮሐም ልጅ ዓዳያ፤ የኢሜር ልጅ፣ የምሺላሚት ልጅ፣ የሜሱላም ልጅ፣ የየሕዜራ ልጅ፣ የዓዲኤል ልጅ መዕሣይ።

ከሌዋውያን ወገን፦ ከሜራሪ ዘሮች የአሳብያ ልጅ፣ የዓዝሪቃም ልጅ፣ የአሱብ ልጅ ሸማያ፣

እንዲሁም ብርቱ የሆኑት ወንድሞቹ 128 ሰዎች፤ የእነርሱም ዋና አለቃ የሐግዶሊም ልጅ ዘብድኤል ነበር።




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች