የወንድሙ የኤሴቅ ወንዶች ልጆች፤ የበኵር ልጁ ኡላም፣ ሁለተኛ ልጁ ኢያስ፣ ሦስተኛ ልጁ ኤሊፋላት።
ኤሴል ስድስት ወንዶች ልጆች ነበሩት፤ ስማቸውም፦ ዓዝሪቃም፣ ቦክሩ፣ እስማኤል፣ ሸዓርያ፣ አብድዩ፣ ሐናን ይባላል፤ እነዚህ ሁሉ የኤሴል ልጆች ናቸው።
የኡላም ልጆች በቀስት መንደፍ የሚችሉ ብርቱ ተዋጊዎች ነበሩ፤ እነርሱም በአጠቃላይ ቍጥራቸው አንድ መቶ ኀምሳ ወንዶች ልጆችና የልጅ ልጆች ነበሯቸው። እነዚህ ሁሉ የብንያም ትውልዶች ነበሩ።