እነዚህ ሁሉ በየትውልድ ሐረጋቸው የተቈጠሩ አለቆችና የቤተ ሰብ መሪዎች ሲሆኑ፣ የሚኖሩትም በኢየሩሳሌም ነበረ።
ያሬሽያ፣ ኤልያስና፣ ዝክሪ የይሮሐም ወንዶች ልጆች ነበሩ።
የገባዖን አባት ይዒኤል በገባዖን ኖረ። የሚስቱም ስም መዓካ ይባላል።
የሳምአን አባት ሚቅሎት ነበሩ። እነርሱም ደግሞ ከሥጋ ዘመዶቻቸው ጋራ በኢየሩሳሌም አቅራቢያ ይኖሩ ነበር።
በኢየሩሳሌም ይኖሩ የነበሩ የይሁዳ፣ የብንያም፣ የኤፍሬምና የምናሴ ነገዶች የሚከተሉት ናቸው፤
እነዚህ ሁሉ የሌዋውያን ቤተ ሰብ አለቆች ሲሆኑ፣ በትውልድ ሐረጋቸው መሠረት ተመዘገቡ፤ የሚኖሩትም በኢየሩሳሌም ነበረ።
ከብንያማውያን፦ የሐስኑአ ልጅ፣ የሆዳይዋ ልጅ፣ የሜሱላም ልጅ ሰሉ።
በዚህ ጊዜ የሕዝቡ መሪዎች መኖሪያቸውን በኢየሩሳሌም አደረጉ፤ ከቀረው ሕዝብ ከዐሥር አንዱ እጅ በቅድስቲቱ ከተማ በኢየሩሳሌም፣ የቀሩት ዘጠኙ እጅ ደግሞ በየራሳቸው ከተሞች እንዲኖሩ ዕጣ ተጣጣሉ።
ነገር ግን የይሁዳ ዘሮች በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ኢያቡሳውያን ከቦታቸው ሊያስለቅቋቸው አልቻሉም፤ ኢያቡሳውያንም እስከ ዛሬ ድረስ ከይሁዳ ሕዝብ ጋራ በኢየሩሳሌም ዐብረው ይኖራሉ።
ጼላ ኤሌፍ፣ የኢያቡሳውያን ከተማ ኢየሩሳሌም፣ ጊብዓ እንዲሁም ቂርያት ነበሩ፤ እነዚህም ከነመንደሮቻቸው ዐሥራ አራት ከተሞች ናቸው። እንግዲህ የብንያም ነገድ በየጐሣቸው የወረሱት ይህ ነበር።
የብንያም ልጆች በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን ኢያቡሳውያንን ከዚያ ሊያስወጧቸው አልቻሉም፤ ስለዚህ ኢያቡሳውያን እስከ ዛሬ ድረስ ከብንያማውያን ጋራ በዚያ ዐብረው ይኖራሉ።