በትውልድ ሐረግ መዝገባቸውም ውስጥ የየቤተ ሰባቸው አለቆችና ሃያ ሺሕ ሁለት መቶ ተዋጊዎች ተመዝግበዋል።
የይዲኤል ልጅ፤ ቢልሐን። የቢልሐን ወንዶች ልጆች፤ የዑስ፣ ብንያም፣ ኤሁድ፣ ክንዓና፣ ዜታን፣ ተርሴስ፣ አኪሳአር፤
የቤኬር ወንዶች ልጆች፤ ዝሚራ፣ ኢዮአስ፣ አልዓዛር፣ ኤልዮዔናይ፣ ዖምሪ፣ ኢያሪሙት፣ አብያ፣ ዓናቶት፣ ዓሌሜት፤ እነዚህ ሁሉ የቤኬር ልጆች ነበሩ።