የቤላ ወንዶች ልጆች፤ ኤሴቦን፣ ኦዚ፣ ዑዝኤል፣ ለኢያሪሙት፣ ዒሪ፤ በአጠቃላይ ዐምስት ሲሆኑ፣ የቤተ ሰብ አለቆች ናቸው፤ በትውልድ ሐረግ መዝገባቸው ሃያ ሁለት ሺሕ ሠላሳ አራት ተዋጊ ሰዎች ተመዝግበዋል።
ሦስቱ የብንያም ወንዶች ልጆች፤ ቤላ፣ ቤኬር፣ ይዲኤል።
የቤኬር ወንዶች ልጆች፤ ዝሚራ፣ ኢዮአስ፣ አልዓዛር፣ ኤልዮዔናይ፣ ዖምሪ፣ ኢያሪሙት፣ አብያ፣ ዓናቶት፣ ዓሌሜት፤ እነዚህ ሁሉ የቤኬር ልጆች ነበሩ።