ከይሳኮር ጐሣዎች ሁሉ የተመዘገቡት ተዋጊዎች የቤተ ሰቦቹ ትውልድ ቍጥር በአጠቃላይ ሰማንያ ሰባት ሺሕ ነበሩ።
ብዙ ሚስቶችና ልጆች ስለ ነበሯቸው፣ ከቤተ ሰባቸው የትውልድ ሐረግ ለውጊያ ብቁ የሆኑ ሠላሳ ስድስት ሺሕ ሰዎች ነበሯቸው።
ሦስቱ የብንያም ወንዶች ልጆች፤ ቤላ፣ ቤኬር፣ ይዲኤል።