እነዚህ ሁሉ የአሴር ዘሮች ናቸው፤ እነርሱም የቤተ ሰብ አለቆች፣ ምርጥ ሰዎች፣ ብርቱ ተዋጊዎችና ድንቅ መሪዎች ነበሩ። በትውልድ መዝገባቸው እንደ ተጻፈው ለውጊያ ብቁ የሆኑት ወንዶች ቍጥር ሃያ ስድስት ሺሕ ነበር።
የዑላ ወንዶች ልጆች፤ ኤራ፣ ሐኒኤል፣ ሪጽያ።
ብንያም የበኵር ልጁን ቤላን፣ ሁለተኛ ልጁን አስቤልን፣ ሦስተኛ ልጁን አሐራን፣
ብንያማውያንም ከመላው የጊብዓ ነዋሪዎች መካከል ከተመረጡት ሰባት መቶ ሰዎች ሌላ፣ ሰይፍ የታጠቁ ሃያ ስድስት ሺሕ ሰዎች በአንድ አፍታ ከየከተሞቻቸው በተጨማሪ አሰባሰቡ።