ልጁ ነዌ፣ ልጁ ኢያሱ።
ልጁ ለአዳን፣ ልጁ ዓሚሁድ፣ ልጁ ኤሊሳማ፣
ከዚያም ሙሴ ከረዳቱ ከኢያሱ ጋራ ዐብሮ ሄደ፤ ሙሴም ወደ እግዚአብሔር ተራራ ወጣ።
ኢያሱ የሕዝቡን የጩኸት ድምፅ በሰማ ጊዜ ሙሴን፣ “በሰፈሩ ውስጥ የጦርነት ድምፅ አለ አለው።”
ከወጣትነቱ ጀምሮ የሙሴ ረዳት የነበረው የነዌ ልጅ ኢያሱም ተነሥቶ፣ “ጌታዬ ሙሴ ሆይ፤ ከልክላቸው እንጂ” ሲል ተናገረ።
እንግዲህ ምድሪቱን እንዲሰልሉ ሙሴ የላካቸው ሰዎች ስም ይህ ነው። ሙሴ ለነዌ ልጅ ለአውሴ፣ “ኢያሱ” የሚል ስም አወጣለት።
ከኤፍሬም ነገድ፣ የነዌ ልጅ አውሴ፤
ምድሪቱን ከሰለሏት መካከል የነበሩት የነዌ ልጅ ኢያሱና የዮፎኒ ልጅ ካሌብ ልብሳቸውን ቀደዱ፤
ስለዚህም እግዚአብሔር ሙሴን እንዲህ አለው፤ “መንፈስ ቅዱስ ያደረበትን የነዌን ልጅ ኢያሱን ወስደህ እጅህን ጫንበት።
አባቶቻችንም ድንኳኗን ከተቀበሉ በኋላ፣ እግዚአብሔር በኢያሱ መሪነት ያሳደዳቸውን የአሕዛብን አገር በወረሱ ጊዜ ይዘዋት ገቡ፤ እስከ ዳዊትም ዘመን ድረስ በምድሪቱ ተቀመጠች፤
እግዚአብሔርም ለነዌ ልጅ ለኢያሱ፣ “በርታ፤ ደፋር ሁን፤ የእስራኤልን ልጆች በመሐላ ቃል ወደ ገባሁላቸው ምድር ታስገባቸዋለህና፤ እኔም ከአንተ ጋራ እሆናለሁ” በማለት ትእዛዝ ሰጠው።
ኢያሱ ዕረፍትን ሰጥቷቸው ቢሆን ኖሮ፣ ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር ስለ ሌላ ቀን ባልተናገረ ነበር።