Biblia Todo Logo
ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች
- ማስታወቂያዎች -



1 ዜና መዋዕል 7:24

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ሴት ልጁ ስሟ ሲአራ ይባላል፤ እርሷም የታችኛውንና የላይኛውን ቤትሖሮንንና ኡዜንሼራን የተባሉትን ከተሞች የቈረቈረች ናት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሰሎሞንም ጌዝርን መልሶ ሠራት፤ እንዲሁም የታችኛውን ቤትሖሮንን፣

ከዚያም ወደ ሚስቱ ገብቶ ተኛ፤ እርሷም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች፤ በቤተ ሰቡ ላይ ከደረሰው መከራ የተነሣ ስሙን በሪዓ አለው።

ልጁ ፋፌ፣ ልጁ ሬሴፍ፣ ልጁ ቴላ፣ ልጁ ታሐን፣

እንዲሁም የላይኛውን ቤትሖሮንና የታችኛውን ቤትሖሮን የተመሸጉ ከተሞች አድርጎ ከቅጥሮቻቸው፣ ከበሮቻቸውና ከመዝጊያዎቻቸው ጋራ ሠራ።

እግዚአብሔርም የአሞራውያንን ነገሥታት በእስራኤል ፊት አሸበራቸው፤ በገባዖን እጅግ መታቸው፤ ወደ ቤትሖሮን በሚያስወጣውም መንገድ ሽቅብ ተከተላቸው፤ እስከ ዓዜቅና እስከ መቄዳም ድረስ አሳድዶ መታቸው።

በዚያም በምዕራብ በኩል ቍልቍል ወደ የፍሌጣውያን ግዛት እስከ ታችኛው ቤትሖሮን ምድር ይወርድና ወደ ጌዝር ዘልቆ ባሕሩ ላይ ይቆማል።

ለኤፍሬም ወገን በየጐሣ በየጐሣቸው የተሰጣቸው ድርሻ ይህ ነው፤ ድንበሩ በምሥራቅ በኩል ከአጣሮት አዳር ተነሥቶ እስከ ላይኛው ቤትሖሮን ይወጣና፣




ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች