አባታቸውም ኤፍሬም ብዙ ቀን አለቀሰላቸው፤ ዘመዶቹም መጥተው አጽናኑት።
ከዚህ በኋላ ያዕቆብ ልብሱን ቀደደ፤ ማቅም ለብሶ ስለ ልጁ ብዙ ቀን አለቀሰ፤
ወንዶችና ሴቶች ልጆቹም ሁሉ ሊያጽናኑት መጡ፤ እርሱ ግን ሊጽናና ባለመቻሉ “በሐዘን እንደ ተኰራመትሁ ልጄ ወዳለበት መቃብር እወርዳለሁ” አለ። ስለ ልጁም አለቀሰ።
ልጁ ዛባድ፣ ልጁ ሹቱላ። ኤድርና ኤልዓድ ከብቶች ለመስረቅ በወረዱ ጊዜ፣ የአገሩ ተወላጆች በሆኑት በጋት ሰዎች ተገደሉ።
ከዚያም ወደ ሚስቱ ገብቶ ተኛ፤ እርሷም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች፤ በቤተ ሰቡ ላይ ከደረሰው መከራ የተነሣ ስሙን በሪዓ አለው።
ሦስቱ የኢዮብ ወዳጆች ቴማናዊው ኤልፋዝ፣ ሹሐዊው በልዳዶስ፣ ናዕማታዊውም ሶፋር በኢዮብ ላይ የደረሰውን መከራ ሁሉ በሰሙ ጊዜ፣ ሄደው ሊያስተዛዝኑትና ሊያጽናኑት በመስማማት ከየመኖሪያቸው በአንድነት መጡ።
ብዙዎች አይሁድም ማርታንና ማርያምን ስለ ወንድማቸው ሞት ሊያጽናኗቸው መጥተው ነበር፤