የኡላም ወንድ ልጅ፤ ባዳን፤ እነዚህ የምናሴ ልጅ፣ የማኪር ልጅ፣ የገለዓድ ወንዶች ልጆች ናቸው።
የኤፍሬምንም የልጅ ልጆች እስከ ሦስት ትውልድ ድረስ አየ። የምናሴ ልጅ ማኪር የወለዳቸውም ልጆች በዮሴፍ ጭን ላይ ተወለዱ።
የማኪር ሚስት መዓካ ወንድ ልጅ ወለደች፤ ስሙንም ፋሬስ አለችው። የወንድሙም ስም ሱሮስ ይባላል፤ ወንዶች ልጆቹም ኡላምና ራቄም ነበሩ።
እኅቱ መለኬት ኢሱድን፣ አቢዔዝርንና ማሕላን ወለደች።
ከዚያም እግዚአብሔር ይሩባኣልን፣ ባርቅን፣ ዮፍታሔንና ሳሙኤልን ልኮ ያለ ሥጋት ትኖሩ ዘንድ በዙሪያችሁ ካሉት ጠላቶቻችሁ እጅ ታደጋችሁ።