ከዮርዳኖስ ወንዝ ማዶ ከኢያሪኮ በስተምሥራቅ ከሚገኘው ከሮቤል ነገድ፣ በምድረ በዳ የሚገኘውን ቦሶርን፣ ያሀጽ፣
ከሌዋውያን የቀሩት የሜራሪ ጐሣዎች ደግሞ ከዚህ የሚከተለውን ወሰዱ፤ ከዛብሎን ነገድ ዮቅኒዓምን፣ ቀርታህን፣ ሬሞንና፣ ታቦርን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ።
ቅዴሞትንና ሜፍዓትን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ፤
እንደዚሁም ከዮርዳኖስ ማዶ ከኢያሪኮ በስተምሥራቅ በሮቤል ነገድ ይዞታ ውስጥ ከፍታ ባለው ምድረ በዳ ያለችውን ቦሶርን፣ በጋድ ነገድ ይዞታ ውስጥ ባለችው በገለዓድ የምትገኘውን ራሞትንና በምናሴ ነገድ ይዞታ ውስጥ በባሳን የምትገኘውን ጎላንን ለዩ።