እንዲሁም እስራኤላውያን ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ድርሻ ላይ ዓኔርና ቢልዓም የተባሉትን ከተሞች ከነመሰማሪያዎቻቸው ወስደው ለቀሩት የቀዓት ጐሣዎች ሰጧቸው።
ኤሎንንና ጋትሪሞን ከነመሰማሪያዎቻቸው ሰጧቸው።
ጌርሶናውያን ከዚህ የሚከተሉትን ከተሞች ወሰዱ፤ ከምናሴ ነገድ እኩሌታ፣ በባሳን የሚገኘውን ጎላንና አስታሮትን ከነመሰማሪያዎቻቸው ወሰዱ፤
እንዲሁም በይሳኮርና በአሴር ውስጥ ቤትሳን፣ ይብለዓም፣ የዶር ሕዝብ፣ ዓይንዶር፣ ታዕናክና መጊዶ በዙሪያቸው ካሉ ሰፈሮቻቸው ጋራ የምናሴ ነበሩ፤ ሦስተኛውም ናፎት ነው።
ከምናሴ ነገድ፣ እኩሌታ ደግሞ ታዕናክና ጋትሪሞን ከነመሰማሪያዎቻቸው ሁለት ከተሞች ተሰጧቸው።