ለአንዳንድ የቀዓት ጐሣዎችም ከኤፍሬም ነገድ ድርሻ ላይ የሚኖሩበት ከተማ ተሰጣቸው።
ለቀሩት የቀዓት ዘሮች ደግሞ ከምናሴ ነገድ እኩሌታ ድርሻ ዐሥር ከተሞች ተሰጧቸው።
በኰረብታማው በኤፍሬም ምድር የሚገኙትን የመማፀኛ ከተሞች ሴኬምን፣ ጌዝርን፣
ከተሞቹም በምድረ በዳው በከፍተኛ ቦታ ላይ የምትገኘው ቦሶር ለሮቤላውያን፣ በገለዓድ የምትገኘው ራሞት ለጋዳውያን፣ በባሳን ያለችው ጎላን ለምናሴያውያን ነበሩ።