መኖሪያዎቻቸው እንዲሆኑ የተመደቡላቸው ቦታዎች እነዚህ ናቸው፦ የመጀመሪያው ዕጣ የእነርሱ ስለ ሆነ፣ ከቀዓት ጐሣ ለሆኑት ለአሮን ዘሮች የተመደቡላቸው መኖሪያዎች እነዚህ ነበሩ።
እነዚህ የእስማኤል ልጆች ነበሩ፤ እነርሱም በኖሩባቸውና በሰፈሩባቸው ቦታዎች የዐሥራ ሁለት ነገድ አለቆች ስሞች ናቸው።
ልጁ ሳዶቅ፣ ልጁ አኪማአስ።
የእንበረማውያን፣ የይስዓራውያን፣ የኬብሮናውያንና የዑዝኤላውያን ጐሣዎች ከቀዓት ወገን ናቸው፤ እነዚህ የቀዓት ጐሣዎች ነበሩ።
ምድያማውያኑ የሚኖሩባቸውን ከተሞች ሁሉ ሰፈሮቻቸውንም በሙሉ አቃጠሉ።
እነዚህም ከተሞች የሌዊ ልጆች፣ የቀዓት ጐሣዎች ለሆኑት ለአሮን ዝርያዎች ተመደቡ፤ ይህም የሆነው የመጀመሪያው ዕጣ ለእነርሱ ስለ ወጣላቸው ነበር፤