የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ ባዘዘው መሠረት፣ ስለ እስራኤል ማስተስረያ በቅድስተ ቅዱሳኑ ውስጥ የሚከናወነውን ተግባር ሁሉ፣ በመሠዊያው ላይ የሚቃጠል መሥዋዕትና በዕጣኑ መሠዊያ ላይ የሚቀርበውን መሥዋዕት የሚያቀርቡት ግን አሮንና ዘሮቹ ብቻ ነበሩ።
ሌዋውያን ወንድሞቻቸው ግን የእግዚአብሔርን ቤት የማደሪያ ድንኳን ተግባር እንዲያከናውኑ ተመድበው ነበር።
ለሰውየውም በመራራት፣ ‘ቤዛ አግኝቼለታለሁና፣ ወደ ጕድጓድ እንዳይወርድ አድነው’ ቢለው፣
ለክህነታቸውና ለመቀደሳቸው ማስተስረያ የሆኑትን እነዚህን መሥዋዕቶች ይብሉ፤ የተቀደሱ ስለ ሆኑ ሌላ ማንም አይብላቸው።
ወይፈኑን በእግዚአብሔር ፊት ይረደው፤ ካህናቱ የአሮን ልጆችም ደሙን አምጥተው በመገናኛው ድንኳን ደጃፍ ባለው በመሠዊያው ዙሪያ ሁሉ ይርጩት።
ለኀጢአት መሥዋዕት ባቀረበው ወይፈን ላይ እንዳደረገው ሁሉ፣ በዚህኛውም ወይፈን ያድርግ፤ በዚህም መሠረት ካህኑ ስለ ሕዝቡ ያስተሰርያል፤ እነርሱም ይቅር ይባላሉ።
ካህኑም ለመላው የእስራኤል ማኅበረ ሰብ ያስተሰርያል፤ እነርሱም ይቅር ይባላሉ፤ ምክንያቱም ባለማወቅ የተፈጸመ ስለ ሆነና ስለ ስሕተታቸውም በእሳት የሚቃጠል መሥዋዕትና የኀጢአት መሥዋዕት ለእግዚአብሔር ስላቀረቡ ነው።
ሙሴም ቆሬን እንዲህ አለው፤ “አንተና ተከታዮችህ እንዲሁም አሮን ነገ በእግዚአብሔር ፊት ትቀርባላችሁ።
እግዚአብሔር እንደ ተናገረው የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ በሞዓብ ምድር ሞተ።
የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ ከሞተ በኋላ፣ እግዚአብሔር የሙሴን አገልጋይ የነዌን ልጅ ኢያሱን እንዲህ አለው፤