እነርሱም ሰሎሞን የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ በኢየሩሳሌም እስኪሠራ ድረስ፣ በማደሪያው፣ ይኸውም በመገናኛው ድንኳን ፊት ሆነው እየዘመሩ ያገለግሉ ነበር፤ አገልግሎታቸውንም የሚያከናውኑት በወጣላቸው ደንብ መሠረት ነው።
ዮሐናን ዓዛርያስን ወለደ፤ እርሱም ሰሎሞን በኢየሩሳሌም ባሠራው ቤተ መቅደስ በክህነት ያገለገለ ነበር፤
ታቦቱ ከገባ በኋላ፣ ዳዊት የመዘምራን አለቃ አድርጎ በእግዚአብሔር ቤት የሾማቸው ሰዎች እነዚህ ናቸው፤
ከወንዶች ልጆቻቸው ጋራ ሆነው ያገለገሉ ሰዎች እነዚህ ናቸው፤ ከቀዓታውያን ልጆች፤ ዘማሪው ኤማን፣ የኢዮኤል ልጅ፣ የሳሙኤል ልጅ፣
የሌዋውያን ቤተ ሰብ አለቆች የነበሩት መዘምራኑ ደግሞ በቤተ መቅደሱ ክፍሎች ውስጥ እንዲኖሩና ከሌላው ሥራ ሁሉ ነጻ እንዲሆኑ ተደርጎ ነበር፤ ምክንያቱም ቀንና ሌሊት የሚሠሩት ሥራ ነበራቸው።
ሕዝቅያስ ካህናቱና ሌዋውያኑ የሚቃጠል መሥዋዕትና የኅብረት መሥዋዕት እንዲያቀርቡ፣ እንዲያገለግሉና እንዲያመሰግኑ እንዲሁም በእግዚአብሔር ማደሪያ ደጆች ውዳሴውን እንዲዘምሩ፣ ካህናትንም ሆኑ ሌዋውያንን እያንዳንዳቸውን እንደየተግባራቸው በየክፍሉ መደባቸው።
መዘምራኑ የአሳፍ ዘሮች በዳዊት፣ በአሳፍ፣ በኤማንና በንጉሡ ባለራእይ በኤዶታም በተሰጠው መመሪያ መሠረት በቦታቸው ነበሩ። በእያንዳንዱ በር ላይ የነበሩት በር ጠባቂዎችም ሌዋውያን ወገኖቻቸው ስላዘጋጁላቸው፣ ከጥበቃ ቦታቸው መለየት አያስፈልጋቸውም ነበር።
በሙሴ መጽሐፍ በተጻፈው መሠረት በኢየሩሳሌም ላለው ለአምላክ አገልግሎት ካህናቱን በየማዕረጋቸው፣ ሌዋውያኑንም በየክፍላቸው መደቧቸው።
በውስጠኛው አደባባይ፣ ከውስጠኛው በር ውጭ፣ ሁለት ክፍሎች ነበሩ፤ አንዱ በደቡብ ትይዩ በሰሜን በር በኩል ሲሆን፣ ሌላው በሰሜን ትይዩ በደቡብ በር በኩል ነበር።