የሳሙኤል ወንዶች ልጆች፤ የበኵር ልጁ ኢዮኤል፣ ሁለተኛው ልጁ አብያ።
ልጁ ኤልያብ፣ ልጁ ይሮሐም፣ ልጁ ሕልቃና፣ ልጁ ሳሙኤል።
የሜራሪ ዘሮች፤ ሞሖሊ፣ ልጁ ሎቤኒ፣ ልጁ ሰሜኢ፣ ልጁ ዖዛ፣
ከወንዶች ልጆቻቸው ጋራ ሆነው ያገለገሉ ሰዎች እነዚህ ናቸው፤ ከቀዓታውያን ልጆች፤ ዘማሪው ኤማን፣ የኢዮኤል ልጅ፣ የሳሙኤል ልጅ፣
የበኵር ልጁ ኢዮኤል ሲሆን፣ ሁለተኛው ልጁ አብያ ነበረ፤ እነርሱም በቤርሳቤህ ይፈርዱ ነበር።