የኢዩኤል ልጅ፣ የሽማዕ ልጅ፣ የዖዛዝ ልጅ ቤላ። እነዚህ ከአሮዔር እስከ ናባውና እስከ በኣልሜዎን ድረስ በሚገኘው ምድር ላይ ሰፈሩ።
የኢዩኤል ዘሮች፤ ልጁ ሸማያ፣ ልጁ ጎግ፣ ልጁ ሰሜኢ፣
ዲቦን ወደ መቅደሱ ወጣ፤ ሊያለቅስም ወደ ኰረብታው ሄደ፤ ሞዓብ ስለ ናባው፣ ስለ ሜድባም ዋይታ ያሰማል፤ ራስ ሁሉ ተመድምዷል፤ ጢምም ሁሉ ተላጭቷል።
የአሮኤር ከተሞች ባድማ ይሆናሉ፤ የመንጎች መሰማሪያ ይሆናሉ፤ የሚያስፈራቸውም የለም።
በምድሪቱ ድንበር ላይ ካሉትና ክብሯ ከሆኑት ከተሞች ከቤትየሺሞት፣ ከበኣልሜዎንና ከቂርያታይም ጀምሬ የሞዓብን ዐምባ እገልጣለሁ።
የጋድ ልጆች፤ ዲቦንን፣ አጣሮትን፣ አሮዔርን፣
እንዲሁም ስማቸው የተለወጠውን ናባውን፣ በኣልሜዎንን፣ ሴባማንን ዐደሱ፤ ላደሷቸውም ከተሞች ስም አወጡላቸው።
“ከኢያሪኮ ማዶ ባለው የሞዓብ ምድር፣ ከዓባሪም ተራሮች አንዱ ወደ ሆነው ወደ ናባው ተራራ ወጥተህ ለእስራኤላውያን ርስት አድርጌ የምሰጣትን የከነዓንን ምድር አሻግረህ ተመልከት።
ሙሴ ከሞዓብ ሜዳ ተነሥቶ ለኢያሪኮ ትይዩ ወደ ሆነው ፈስጋ ጫፍ፣ ወደ ናባው ተራራ ወጣ። በዚያም እግዚአብሔር ምድሪቱን ሁሉ አሳየው፤ ይኸውም ከገለዓድ እስከ ዳን፣
መቀመጫውን በሐሴቦን አድርጎ የገዛው የአሞራውያን ንጉሥ ሴዎን፣ ከአርኖን ሸለቆ ዳርቻ ላይ ካለችው ከአሮዔር ማለት ከሸለቆው መካከል አንሥቶ፣ የአሞናውያን ወሰን እስከ ሆነው እስከ ያቦቅ ወንዝ ድረስ ገዝቷል፤ ይህም የገለዓድን እኩሌታ ይጨምራል።
ሐሴቦንና በደጋው ላይ ያሉትን ከተሞቿን በሙሉ፣ እንዲሁም ዲቦንን፣ ባሞትባኣልን፣ ቤትበኣልምዖን፣